ክርስቲያናዊ ሕይወት
ይሖዋን ለማገልገል ምረጡ
በእውነት ቤት ውስጥ ያደግክ ወጣት አሊያም ደግሞ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ነህ? ከሆነ የመጠመቅ ግብ አለህ? ለመሆኑ የመጠመቅ ግብ ማውጣት ያለብህ ለምንድን ነው? ራስን መወሰንና መጠመቅ ከይሖዋ ጋር ልዩ ዝምድና ለመመሥረት ያስችላል። (መዝ 91:1) እንዲሁም መዳን ያስገኛል። (1ጴጥ 3:21) ታዲያ እድገት አድርገህ እዚህ ግብ ላይ መድረስ የምትችለው እንዴት ነው?
እውነትን ማግኘትህን አረጋግጥ። ጥያቄ ሲፈጠርብህ ምርምር አድርግ። (ሮም 12:2) ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልግህን አቅጣጫዎች ለይተህ እወቅ፤ እንዲሁም ይሖዋን ለማስደሰት ያለህ ፍላጎት አስፈላጊውን ማስተካከያ ለማድረግ ያነሳሳህ። (ምሳሌ 27:11፤ ኤፌ 4:23, 24) እርዳታ ለማግኘት ምንጊዜም ወደ ይሖዋ ጸልይ። ይሖዋ ኃያል በሆነው ቅዱስ መንፈሱ ተጠቅሞ እንደሚያጠነክርህና እንደሚደግፍህ እርግጠኛ ሁን። (1ጴጥ 5:10, 11) ይሖዋን ማገልገል ከሁሉ የተሻለ የሕይወት ጎዳና ነው። በመሆኑም እዚህ ግብ ላይ ለመድረስ ስትል የምታደርገው ጥረት መቼም ቢሆን አያስቆጭህም!—መዝ 16:11
ወደ ጥምቀት የሚያደርሰው መንገድ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
አንዳንዶች ለመጠመቅ ሲሉ የትኞቹን እንቅፋቶች መወጣት አስፈልጓቸዋል?
-
ራስህን ለይሖዋ ለመወሰን የሚያነሳሳ እምነት ለማዳበር ምን ሊረዳህ ይችላል?
-
አንዳንዶች ወደ ጥምቀት የሚያደርሱትን እርምጃዎች ለመውሰድ ያነሳሳቸው ምንድን ነው?
-
ይሖዋን ለማገልገል የሚመርጡ ሰዎች ምን በረከት ያገኛሉ?
-
ራስን ወስኖ መጠመቅ ምን ትርጉም አለው?