ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ሌዋውያን የሚያከናውኑት አገልግሎት
ይሖዋ ሌዋውያንን በእስራኤላውያን በኩር ወንዶች ምትክ ወስዷቸዋል (ዘኁ 3:11-13፤ it-2 683 አን. 3)
ሌዋውያን ልዩ መብቶች ነበሯቸው (ዘኁ 3:25, 26, 31, 36, 37፤ it-2 241)
ሌዋውያን አገልግሎታቸውን በዋነኝነት የሚያከናውኑት ከ30 እስከ 50 ዓመት ባለው የዕድሜ ክልል ውስጥ ሲሆኑ ነው (ዘኁ 4:46-48፤ it-2 241)
በአሮን ቤተሰብ ውስጥ ያሉት ወንዶች የክህነት አገልግሎት ያከናውኑ ነበር። ሌሎቹ ሌዋውያን ደግሞ ካህናቱን ያግዟቸዋል። በዛሬው ጊዜም በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ አንዳንድ ወንዶች ከበድ ያሉ ኃላፊነቶችን ሲወጡ ሌሎች ወንድሞች ደግሞ አስፈላጊ የሆኑ ሌሎች ሥራዎችን ያከናውናሉ።