በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

“ክርስቶስ ያለው ፍቅር ግድ ይለናል።”—2ቆሮ 5:14

ክርስቲያናዊ ሕይወት

በመጋቢት ወይም በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ሆነህ ማገልገል ትችላለህ?

በመጋቢት ወይም በሚያዝያ ረዳት አቅኚ ሆነህ ማገልገል ትችላለህ?

በመታሰቢያው በዓል ሰሞን በይሖዋ አገልግሎት የበለጠ ተሳትፎ ማድረግ ትፈልጋለህ? (2ቆሮ 5:14, 15) መጋቢትና ሚያዝያ ላይ ረዳት አቅኚ የሚሆኑ አስፋፊዎች ለ30 ሰዓት ወይም ለ50 ሰዓት ለማገልገል መምረጥ ይችላሉ። በዚህ ልዩ የአገልግሎት እንቅስቃሴ መካፈል የምትችል ከሆነ ማመልከቻ በመሙላት ለጉባኤህ የአገልግሎት ኮሚቴ መስጠት ትችላለህ። ረዳት አቅኚ ሆነው እንዲያገለግሉ የተፈቀደላቸው አስፋፊዎች ስም በየወሩ ለጉባኤው ይነበባል። ይህም የጉባኤው አስፋፊዎች ከረዳት አቅኚዎቹ ጋር አብረው በማገልገል እንዲያግዟቸው ያደርጋል። ሁላችንም በመታሰቢያው በዓል ሰሞን የምናገኛቸውን አጋጣሚዎች በሙሉ በመጠቀም የስብከት ችሎታችንን እናሻሽል እንዲሁም እርስ በርስ እንበረታታ።—1ተሰ 5:11