በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለሁሉም ሰው ለመስበክ መደራጀት

ለሁሉም ሰው ለመስበክ መደራጀት

ይሖዋ እስራኤላውያንን እንዳደራጃቸው ሁሉ በዛሬው ጊዜ ያሉ ሕዝቦቹንም ፈቃዱን እንዲያደርጉ አደራጅቷቸዋል። በዓለም ዙሪያ የሚገኙ ቅርንጫፍ ቢሮዎች፣ ወረዳዎች፣ ጉባኤዎችና የመስክ አገልግሎት ቡድኖች የስብከቱን ሥራ ለማከናወን ተባብረው ይሠራሉ። ከእኛ የተለየ ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎችን ጨምሮ ለሁሉም ሰው እንሰብካለን።—ራእይ 14:6, 7

ሌሎችን ስለ እውነት ለማስተማር ስትል አዲስ ቋንቋ ለመማር አስበህ ታውቃለህ? አዲስ ቋንቋ ለመማር በቂ ጊዜ ባይኖርህም እንኳ JW Language በተባለው አፕሊኬሽን ተጠቅመህ ቀለል ያለ መግቢያ መማር ትችላለህ። ይህን መግቢያ በአገልግሎት ላይ ስትጠቀም በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩት ክርስቲያኖች ያገኙትን ዓይነት ደስታ ማጣጣም ትችላለህ፤ እነዚህ ክርስቲያኖች ከሌሎች አገሮች የመጡ ሰዎች በየቋንቋቸው “ስለ አምላክ ታላቅ ሥራ” በመስማታቸው እጅግ ሲደነቁ ማየታቸው አስደስቷቸው ነበር።—ሥራ 2:7-11

የይሖዋ ወዳጅ ሁን—በውጭ አገር ቋንቋ መስበክ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • JW Language የተባለው አፕሊኬሽን የሚጠቅምህ በምን ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ነው?

  • ይህ አፕሊኬሽን ካሉት ገጽታዎች መካከል አንዳንዶቹ የትኞቹ ናቸው?

  • ቋንቋቸው ምንም ይሁን ምን ለሁሉም ሰዎች ምሥራቹን መስበክ አለብን

    በክልላችሁ ውስጥ የትኞቹን ቋንቋዎች የሚናገሩ ሰዎች ይገኛሉ?

  • ሌላ ቋንቋ የሚናገር ሰው ለመንግሥቱ መልእክት ፍላጎት ካሳየ ምን ማድረግ ይኖርብሃል?—od 100-101 አን. 39-41