ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የኢዮቤልዩ ዓመት እና ወደፊት የምናገኘው ነፃነት
የኢዮቤልዩ ዓመት እስራኤላውያን በማይወጡት ዕዳ እንዳይዘፈቁና ዕድሜ ልካቸውን ድሃ ሆነው እንዳይኖሩ ያደርግ ነበር (ዘሌ 25:10፤ it-1 871፤ ሽፋኑን ተመልከት)
መሬት ተሸጠ ሲባል ለተወሰነ ጊዜ መከራየቱን የሚያመለክት ነበር፤ ዋጋው የሚተመነው መሬቱ የሚያስገኘውን ሰብል ግምት ውስጥ በማስገባት ነበር (ዘሌ 25:15፤ it-1 1200 አን. 2)
ሕዝቡ ከኢዮቤልዩ ዓመት ጋር በተያያዘ የተሰጣቸውን ሕግ ሲያከብሩ ይሖዋ ይባርካቸው ነበር (ዘሌ 25:18-22፤ it-2 122-123)
በቅርቡ ታማኝ የሰው ልጆች ከኃጢአትና ከሞት ሙሉ በሙሉ ነፃ ስለሚወጡ ከምሳሌያዊው ኢዮቤልዩ የተሟላ ጥቅም ያገኛሉ።—ሮም 8:21
ይሖዋ ቃል የገባልንን ነፃነት ለማግኘት እያንዳንዳችን ምን ማድረግ ይኖርብናል?