በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ እና ኢየሱስ ወደፊት የሚያስገኙልን ነፃነት

ይሖዋ እና ኢየሱስ ወደፊት የሚያስገኙልን ነፃነት

በየዕለቱ ከየትኞቹ ተፈታታኝ ሁኔታዎች ጋር ትታገላለህ? ብዙ ኃላፊነቶች የተደራረቡብህ የቤተሰብ ራስ ነህ? ልጆችሽን ለማሳደግ ደፋ ቀና የምትዪ ነጠላ እናት ነሽ? እኩዮችህ የሚያስቸግሩህ ተማሪ ነህ? የጤና እክል ወይም የዕድሜ መግፋት ከሚያስከትላቸው ችግሮች ጋር እየታገልክ ነው? ሁላችንም የተለያዩ ፈተናዎች ያጋጥሙናል። በርካታ ክርስቲያኖች ደግሞ ብዙ ችግሮች በላይ በላይ ተደራርበውባቸዋል። ሆኖም በቅርቡ ከእነዚህ ችግሮች እንደምንላቀቅ እናውቃለን።—2ቆሮ 4:16-18

እስከዚያው ድረስ ግን ይሖዋ የምናደርገውን ትግል እንደሚረዳልን፣ ታማኝነታችንንና ጽናታችንን እንደሚያደንቅ እንዲሁም ታላቅ በረከት እንዳዘጋጀልን ማወቃችን ያጽናናናል። (ኤር 29:11, 12) ኢየሱስም በግለሰብ ደረጃ ያስብልናል። ክርስቲያናዊ ኃላፊነታችንን ስንወጣ ‘ከእኛ ጋር እንደሚሆን’ ቃል ገብቶልናል። (ማቴ 28:20) በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር ስለምናገኘው ነፃነት ስናሰላስል ተስፋችን ይበልጥ እውን ሆኖ ይታየናል፤ እንዲሁም የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች ለመቋቋም ያለን ቁርጠኝነት ይጠናከራል።—ሮም 8:19-21

አውሎ ነፋሱ ሲቃረብ ኢየሱስን በትኩረት ተመልከቱ!—መንግሥቱ የሚያስገኛቸው በረከቶች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የሰው ልጆች ከአምላክ የራቁት እንዴት ነው? ውጤቱስ ምን ሆነ?

  • ለአምላክ ታማኝ የሆኑ ሰዎች ምን ተስፋ ይጠብቃቸዋል?

  • የሰው ልጆች ይህ አስደናቂ ተስፋ ሊኖራቸው የቻለው እንዴት ነው?

  • በአዲሱ ዓለም ውስጥ አንተ ለማግኘት የምትጓጓው የትኞቹን በረከቶች ነው?

በአዲሱ ዓለም ውስጥ ስትኖር ይታይህ