ክርስቲያናዊ ሕይወት
ወላጆች፣ ለልጆቻችሁ እውቀት አስጨብጧቸው
የምንኖርበት ዓለም ጥሩውን መጥፎ፣ መጥፎውን ደግሞ ጥሩ አስመስሎ ያቀርባል። (ኢሳ 5:20) የሚያሳዝነው፣ አንዳንዶች ይሖዋ የሚጠላቸውን ነገሮች ያደርጋሉ፤ ይህም ተመሳሳይ ፆታ ባላቸው ሰዎች መካከል የሚፈጸምን ተገቢ ያልሆነ ምግባር ይጨምራል። ልጆቻችሁ በመጥፎ ድርጊት እንዲካፈሉ በትምህርት ቤት ባሉ እኩዮቻቸው ወይም በሌሎች ሰዎች ተጽዕኖ ይደረግባቸዋል። ታዲያ ልጆቻችሁ እንደነዚህ ያሉ ፈተናዎችን እንዲቋቋሙ ልታዘጋጇቸው የምትችሉት እንዴት ነው?
ለልጆቻችሁ ስለ ይሖዋ መሥፈርቶች እውቀት አስጨብጧቸው። (ዘሌ 18:3) መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ፆታ ሥነ ምግባር ምን እንደሚል ደረጃ በደረጃና ዕድሜያቸውን ባገናዘበ መልኩ አስተምሯቸው። (ዘዳ 6:7) ራሳችሁን እንደሚከተለው በማለት ጠይቁ፦ ‘ተገቢ የሆኑ የፍቅር መግለጫዎች የትኞቹ እንደሆኑ፣ ልከኝነት የሚንጸባረቅበት አለባበስ አስፈላጊ የሆነው ለምን እንደሆነ እንዲሁም ሌሎች ባሉበት ማድረግ ስለሌለባቸው ነገሮች ልጆቼን አሠልጥኛቸዋለሁ? ልጆቼ አንድ ሰው የብልግና ምስሎችንና ጽሑፎችን (ፖርኖግራፊ) ሊያሳያቸው ቢሞክር ወይም በይሖዋ ፊት ትክክል ያልሆነ ነገር እንዲያደርጉ ቢጠይቃቸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ?’ ልጆቻችሁ ተገቢውን እውቀት ማግኘታቸው ከብዙ ችግር ይጠብቃቸዋል። (ምሳሌ 27:12፤ መክ 7:12) ይሖዋ የሰጣችሁ ውድ ውርሻ የሆኑትን ልጆቻችሁን በማስተማር፣ ለእነሱ ያላችሁን ፍቅር ማሳየት ትችላላችሁ።—መዝ 127:3
እስከ መጨረሻው የሚጸና ቤት ገንቡ—ልጆቻችሁን ‘ከክፉ ነገር’ ጠብቁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
አንዳንዶች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ጉዳዮች ማስተማር የሚከብዳቸው ለምንድን ነው?
-
ወላጆች ልጆቻቸውን “በይሖዋ ተግሣጽና ምክር” ማሠልጠን ያለባቸው ለምንድን ነው?—ኤፌ 6:4
-
የይሖዋ ድርጅት ወላጆች ልጆቻቸውን ስለ ፆታ ጉዳዮች እንዲያስተምሩ ለመርዳት ምን ዝግጅት አድርጓል?—w19.05 12 ሣጥን
-
ልጆቻችሁ ከባድ ችግር ሳያጋጥማቸው በፊት አዘውትራችሁ ልታዋሯቸው የሚገባው ለምንድን ነው?