ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ሳኦል መጀመሪያ ላይ ትሑትና ልኩን የሚያውቅ ሰው ነበር
ሳኦል ልኩን የሚያውቅ ሰው ስለነበር ንግሥናውን ለመቀበል አመንትቷል (1ሳሙ 9:21፤ 10:20-22፤ w20.08 10 አን. 11)
ሳኦል፣ ሌሎች ስለ እሱ መጥፎ ባወሩበት ወቅት በስሜታዊነት እርምጃ አልወሰደም (1ሳሙ 10:27፤ 11:12, 13፤ w14 3/15 9 አን. 8)
ሳኦል የይሖዋ ቅዱስ መንፈስ የሚሰጠውን አመራር ተከትሏል (1ሳሙ 11:5-7፤ w95 12/15 10 አን. 1)
ትሕትና፣ ያገኘነውን መብትም ሆነ ችሎታችንን የይሖዋ ስጦታ አድርገን እንድንመለከተው ይረዳናል። (ሮም 12:3, 16፤ 1ቆሮ 4:7) በተጨማሪም ትሑቶች ከሆንን ምንጊዜም የይሖዋን መመሪያ ለማግኘት ጥረት እናደርጋለን።