ክርስቲያናዊ ሕይወት
ፍጥረት በይሖዋ ጥበብ ላይ ያለንን እምነት ያጠናክርልናል
ይሖዋ አምላካችን፣ ለእኛ የሚበጀው ምን እንደሆነ ምንጊዜም ያውቃል? ምንም ጥርጥር የለውም! ይህን ስለምናምን የሱን መመሪያ በመከተል ጥበብ እንዳለን እናሳያለን። (ምሳሌ 16:3, 9) ይሁንና ይሖዋ የሚሰጠን መመሪያ እኛ ካሰብነው የተለየ በሚሆንበት ወቅት በመመሪያዎቹ ላይ ያለን እምነት ይፈተናል። በፍጥረት ሥራዎቹ ላይ በማሰላሰል በይሖዋ ጥበብ ላይ ያለንን እምነት ማጠናከር እንችላለን።—ምሳሌ 30:24, 25፤ ሮም 1:20
ንድፍ አውጪ አለው? ጉንዳኖች የትራፊክ መጨናነቅን የሚከላከሉበት መንገድ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
አብዛኞቹ ጉንዳኖች በየቀኑ ምን ሥራ ያከናውናሉ?
-
ጉንዳኖች የትራፊክ መጨናነቅን የሚከላከሉት እንዴት ነው?
-
የሰው ልጆች የጉንዳኖችን የትራፊክ ፍሰት በመኮረጅ ምን ጠቃሚ ሐሳቦች ማግኘት ይችላሉ?
ንድፍ አውጪ አለው? የንቦች የበረራ ጥበብ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
የሰው ልጆች ትናንሽ አውሮፕላኖችን ሲያበርሩ ምን ተፈታታኝ ሁኔታ ያጋጥማቸዋል?
-
አንዲት ንብ ስትበር ኃይለኛ ነፋስ አቅጣጫዋን እንዳያስታት ምን ታደርጋለች?
-
የሰው ልጆች፣ ንቦች በደመ ነፍስ ያላቸውን ይህን ጥበብ በመኮረጅ ወደፊት ምን ሊፈለስፉ ይችሉ ይሆናል?
በምትኖርበት አካባቢ፣ የይሖዋን ጥበብ የሚያሳዩ ምን የፍጥረት ሥራዎች ተመልክተሃል?