በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳይህ እርግጠኛ ሁን

ይሖዋ ታማኝ ፍቅር እንደሚያሳይህ እርግጠኛ ሁን

በይሖዋ ፊት ውድ ነህ። (ኢሳ 43:4) ወደ እሱም ሆነ ወደ ድርጅቱ ስቦሃል። ራስህን ለይሖዋ ወስነህ ስለተጠመቅክ የእሱ ንብረት ሆነሃል። ስለዚህ በአስቸጋሪ ጊዜም ጭምር፣ እንደ ልዩ ንብረቱ ይንከባከብሃል። በድርጅቱ አማካኝነት ታማኝ ፍቅር ያሳይሃል።—መዝ 25:10

የይሖዋ ድርጅት በቅርብ ጊዜ ለተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች ምላሽ የሰጠበትን መንገድ መለስ ብለን ስናይ ለይሖዋ ታማኝ ፍቅር ያለን አድናቆት ይጨምራል።

የ2019 የአስተባባሪዎች ኮሚቴ ሪፖርት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የአስተባባሪዎች ኮሚቴ፣ በዓለም ዙሪያ ያሉ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ለአደጋ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት ዝግጁ እንዲሆኑ ያደረገው እንዴት ነው?

  • በኢንዶኔዥያ እና በናይጄርያ ከተፈጠረው ነገር ጋር በተያያዘ የይሖዋ ድርጅት መመሪያና የአደጋ ጊዜ እርዳታ የሰጠው እንዴት ነው?

  • የይሖዋ ድርጅት ለኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምላሽ ከሰጠበት መንገድ ጋር በተያያዘ አንተን ያስገረመህ የቱ ነው?