ክርስቲያናዊ ሕይወት
የአምላክን አስተሳሰብ ለማወቅ ጥረት አድርጉ
በምናደርገው ነገር ሁሉ ይሖዋን ማስደሰት እንፈልጋለን። (ምሳሌ 27:11) ይህንንም ለማድረግ፣ በግልጽ የተቀመጠ መመሪያ ወይም ትእዛዝ በማይኖርበት ጊዜም እንኳ የይሖዋን አስተሳሰብ የሚያንጸባርቅ ውሳኔ ማድረግ ይጠበቅብናል። ታዲያ ይህን ለማድረግ ምን ይረዳናል?
ቋሚ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም ይኑራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስን ባነበብን ቁጥር ከይሖዋ ጋር ጊዜ እያሳለፍን እንዳለ ሊቆጠር ይችላል። ይሖዋ ሕዝቡን የያዘበትን መንገድ በማጥናት እንዲሁም በእሱ ዓይን ጥሩ ወይም መጥፎ ያደረጉ ሰዎችን ታሪክ በመመርመር ስለ ይሖዋ አስተሳሰብ መማር እንችላለን። ውሳኔ ማድረግ የሚጠይቅ ሁኔታ ሲያጋጥመን መንፈስ ቅዱስ ከአምላክ ቃል የተማርናቸውን ጠቃሚ ትምህርቶችና መሠረታዊ ሥርዓቶች እንድናስታውስ ይረዳናል።—ዮሐ 14:26
ምርምር አድርግ። ውሳኔ ማድረግ ሲያስፈልጋችሁ ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፦ ‘ስለ ጉዳዩ ይሖዋ ያለውን አመለካከት ለማወቅ የሚረዱኝ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ወይም ዘገባዎች ናቸው?’ ይሖዋ እንዲረዳችሁ ጸልዩ፤ እንዲሁም ለእናንተ ሁኔታ የሚሠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ለማግኘትና በሥራ ላይ ለማዋል እንድትችሉ በቋንቋችሁ የተዘጋጁ የምርምር መሣሪያዎችን ተጠቀሙ።—መዝ 25:4
‘በጽናት ሩጡ’—ገንቢ ምግብ ተመገቡ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
በቪዲዮው ላይ የታየችው ወጣት እህት ምን ዓይነት ተጽዕኖ መቋቋም አስፈልጓታል?
-
እናንተስ እንዲህ ዓይነት ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም የምርምር መሣሪያዎችን መጠቀም የምትችሉት እንዴት ነው?
-
ጊዜ ወስደን ምርምርና የግል ጥናት ማድረጋችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?—ዕብ 5:13, 14