ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የአምላክን ፈቃድ ለማድረግ ያላችሁን ፍላጎት አጠናክሩ
ሳኦል ታዛዥ ባለመሆኑ ይሖዋ ንቆታል (1ዜና 10:13, 14)
ይሖዋ በሳኦል ምትክ ንጉሥ እንዲሆን ዳዊትን መርጦታል (1ዜና 11:3)
ከሳኦል በተለየ መልኩ ዳዊት በይሖዋ ሕጎችና መሠረታዊ ሥርዓቶች ለመመራት ፈቃደኛ ነበር (1ዜና 11:15-19፤ w12 11/15 6 አን. 12-13)
ዳዊት የአምላክን ፈቃድ ማድረግ ያስደስተው ነበር። (መዝ 40:8) እኛም እንደ ዳዊት፣ ይሖዋ ለነገሮች ያለው ዓይነት አመለካከት በማዳበር ትክክል የሆነውን ነገር ለማድረግ ያለንን ፍላጎት ማሳደግ እንችላለን።—መዝ 25:4፤ w18.06 17 አን. 5-6