ከጥር 2-8
2 ነገሥት 22–23
መዝሙር 28 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ትሑት መሆን ያለብን ለምንድን ነው?”፦ (10 ደቂቃ)
መንፈሳዊ ዕንቁዎች፦ (10 ደቂቃ)
2ነገ 23:24, 25—የኢዮስያስ ምሳሌ ጥሩ አስተዳደግ ለሌላቸው ክርስቲያኖች ምን ማበረታቻ ይሰጣል? (w01 4/15 26 አን. 3-4)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ይሖዋን፣ የመስክ አገልግሎትን ወይም ሌሎች ነገሮችን በተመለከተ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ) 2ነገ 23:16-25 (th ጥናት 2)
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
መመሥከር—ቪዲዮ፦ (5 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። መመሥከር፦ ጸሎት—መዝ 65:2 የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ውይይቱ ቆም ሲል ቪዲዮውን አቁመህ በቪዲዮው ላይ ያሉትን ጥያቄዎች ለአድማጮች አቅርብ።
መመሥከር፦ (3 ደቂቃ) የውይይት ናሙናውን ርዕሰ ጉዳይ ተጠቀም። (th ጥናት 1)
መመሥከር፦ (5 ደቂቃ) በውይይት ናሙናው ርዕሰ ጉዳይ ጀምር፤ ከዚያም ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን ብሮሹር ምዕራፍ 01ን ተጠቅመህ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት አስጀምር። (th ጥናት 16)
ክርስቲያናዊ ሕይወት
ትሑታን ወይስ ትዕቢተኞች? (ያዕ 4:6)፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦ በትሕትናና በትዕቢት መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው? ሙሴ ከተወው ምሳሌ ምን እንማራለን? ትሑት ለመሆን የቆረጣችሁት ለምንድን ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 33
የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 23 እና ጸሎት