ክርስቲያናዊ ሕይወት
ድንገት ለሚያጋጥም የጤና ችግር ከወዲሁ ተዘጋጁ
መዘጋጀት ለምን አስፈለገ? ድንገተኛ የጤና ችግር ወይም ሆስፒታል የሚያስተኛ ሁኔታ በማንኛውም ጊዜ እንዲሁም ባልጠበቅነው ሰዓት ሊያጋጥመን ይችላል። በመሆኑም ከሁሉ የተሻለ ሕክምና ማግኘት እንድትችሉ ድንገተኛ ሁኔታ ከመፈጠሩ በፊት አቅማችሁ በፈቀደ መጠን ተዘጋጁ። እንዲህ ማድረጋችሁ ለሕይወትም ሆነ ይሖዋ ስለ ደም ላወጣው ሕግ ያላችሁን አክብሮት ያሳያል።—ሥራ 15:28, 29
መዘጋጀት የምትችሉት እንዴት ነው?
-
የሕክምና መመሪያ ካርድ (DPA) በጸሎት ታግዛችሁ በጥንቃቄ ሙሉ። a የተጠመቁ አስፋፊዎች የሕክምና መመሪያ ካርዱን ከጽሑፍ አገልጋዩ ማግኘት ይችላሉ፤ በተጨማሪም ለትናንሽ ልጆቻቸው የመታወቂያ ካርድ (ic) መውሰድ ይችላሉ
-
ነፍሰ ጡር ከሆናችሁ ሽማግሌዎች ለነፍሰ ጡር እናቶች የተሰጠ መረጃ (S-401) የተባለውን ሰነድ እንዲሰጧችሁ ጠይቁ። ሰነዱ በእርግዝና እና በወሊድ ወቅት ሊያጋጥሙ የሚችሉ የሕክምና ጉዳዮችን በተመለከተ ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ ይረዳችኋል
-
ከደም ጋር የተያያዘ ጥያቄ የሚያስነሳ ወይም ሆስፒታል የሚያስተኛ ሕክምና የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ አስቀድማችሁ ለሽማግሌዎቻችሁ አሳውቁ፤ እንዲሁም አንድ የይሖዋ ምሥክር መጥቶ እንዲጠይቃችሁ የምትፈልጉ መሆኑን ለሆስፒታሉ አሳውቁ
ሽማግሌዎች ምን እርዳታ መስጠት ይችላሉ? የሕክምና መመሪያ ካርድ ስትሞሉ ሊረዷችሁ ይችላሉ። ይሁንና በእናንተ ቦታ ሆነው ከሕክምና ጋር የተያያዘ ውሳኔ አያደርጉም፤ ወይም ለግል ምርጫ በተተዉ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን አስተያየት አይሰጡም። (ሮም 14:12፤ ገላ 6:5) ከደም ጋር የተያያዘ ጥያቄ ሊያስነሳ የሚችል የሕክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋችሁ ለጉባኤያችሁ ሽማግሌዎች ከነገራችኋቸው የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴን (HLC) በአፋጣኝ ያነጋግሩላችኋል።
የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴ ምን እርዳታ መስጠት ይችላል? በሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴ ውስጥ የሚያገለግሉ ወንድሞች ደምን አስመልክቶ ያለንን ሃይማኖታዊ አቋም ለሕክምና እና ለሕግ ባለሙያዎች ለማስረዳት ልዩ ሥልጠና ወስደዋል። ያለደም የሚሰጡ አማራጭ ሕክምናዎችን አስመልክቶ ሐኪማችሁን ሊያነጋግሩላችሁ ይችላሉ። ካስፈለገ ደግሞ ተባባሪ ሐኪም ሊያፈላልጉላችሁ ይችላሉ።
ደምን በመጠቀም ከሚሰጡ ሕክምናዎች ጋር በተያያዘ ውሳኔ ማድረግ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ከደም ጋር የተያያዘ ጥያቄ ለሚያስነሳ ድንገተኛ የጤና ችግር ለመዘጋጀት የሚረዳ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
a ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለው መጽሐፍ ምዕራፍ 39 ከደም ጋር የተያያዘ የሕክምና ውሳኔ በምታደርጉበት ጊዜ ሊረዳችሁ ይችላል።