በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከየካቲት 26–መጋቢት 3

መዝሙር 11–15

ከየካቲት 26–መጋቢት 3

መዝሙር 139 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ሰላም በሰፈነበት የአምላክ አዲስ ዓለም ውስጥ ስትኖሩ ይታያችሁ

(10 ደቂቃ)

ሕገ ወጥነት መስፋፋቱ ዓለም በዓመፅ እንዲሞላ አድርጓል (መዝ 11:2, 3w06 5/15 18 አን. 3)

ይሖዋ በቅርቡ ዓመፅን እንደሚያስቆም እርግጠኞች መሆን እንችላለን (መዝ 11:5wp16.4 11)

ይሖዋ በሰጠን የመዳን ተስፋ ላይ ማሰላሰላችን መዳናችን እስኪመጣ ድረስ በትዕግሥት እንድንጠብቅ ይረዳናል (መዝ 13:5, 6w17.08 6 አን. 15)

እንዲህ ለማድረግ ሞክር፦ ሕዝቅኤል 34:25⁠ን አንብብ፤ ከዚያም እዚያ ላይ በተገለጸው ሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ ራስህን ለመሣል ሞክር።—kr 236 አን. 16

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 14:1—እዚህ ላይ የተጠቀሰው ዝንባሌ ክርስቲያኖችን እንኳ ሊያጠቃ የሚችለው እንዴት ነው? (w13 9/15 19 አን. 12)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኝ ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 3)

5. ውይይት መጀመር

(1 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ በመታሰቢያው በዓል ላይ እንዲገኝ ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 4)

6. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ ለመታሰቢያው በዓል ሲጋበዝ ፍላጎት እንዳለው አሳይቷል። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 4)

7. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(5 ደቂቃ) lff ምዕራፍ 13 ማጠቃለያ፣ ክለሳ እና ግብ። ጥናትህ፣ አምላክ ለሐሰት ሃይማኖት ያለውን አመለካከት እንዲገነዘብ ለመርዳት “ምርምር አድርግ” በሚለው ክፍል ውስጥ ካሉት ርዕሶች መካከል አንዱን ተጠቀም። (th ጥናት 12)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 8

8. “ከጦር መሣሪያ ይልቅ ጥበብ ትሻላለች”

(10 ደቂቃ) ውይይት።

በዓለም ዙሪያ የዓመፅ ድርጊቶች እየተበራከቱ ነው። ይሖዋ፣ የሚደርስብንና በዙሪያችን የምናየው ዓመፅ ጭንቀት ሊፈጥርብን እንደሚችል ይረዳል። ጥበቃ ማግኘት እንደምንፈልግም ያውቃል። ይሖዋ እኛን የሚጠብቅበት አንዱ መንገድ በቃሉ በመጽሐፍ ቅዱስ አማካኝነት ነው።—መዝ 12:5-7

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘው ጥበብ ‘ከጦር መሣሪያ የተሻለ ነው።’ (መክ 9:18) የሚከተሉት የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች የዓመፅ ሰለባ እንዳንሆን ሊረዱን የሚችሉት እንዴት እንደሆነ ልብ በሉ።

  • መክ 4:9, 10—አደገኛ በሆኑ ቦታዎችና ሁኔታዎች ውስጥ ብቻችሁን ከመሆን ተቆጠቡ

  • ምሳሌ 22:3—በሰዎች መካከል ስትሆኑ አካባቢያችሁን በንቃት ተከታተሉ

  • ምሳሌ 26:17—በማይመለከታችሁ ጭቅጭቅ ውስጥ አትግቡ

  • ምሳሌ 17:14—አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችል ከጠረጠራችሁ አካባቢውን ለቃችሁ ሂዱ። በተጨማሪም የተቃውሞ ሰልፍ ከሚካሄድባቸው አካባቢዎች ራቁ

  • ሉቃስ 12:15—ንብረታችሁን ለመጠበቅ ስትሉ ሕይወታችሁን ፈጽሞ አደጋ ላይ አትጣሉ

የእምነት የለሾችን ሳይሆን የእምነት ሰዎችን ምሳሌ ተከተሉ—ላሜህን ሳይሆን ሄኖክን የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

የሄኖክ ምሳሌ፣ ዓመፅ በነገሠበት አካባቢ በሚኖረው አባት ውሳኔና ድርጊት ላይ ተጽዕኖ ያሳደረው እንዴት ነው?—ዕብ 11:5

በአንዳንድ ሁኔታዎች ውስጥ አንድ ክርስቲያን ራሱን ወይም ንብረቱን ለመጠበቅ ምክንያታዊ የሆነ እርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልገው ሊሰማው ይችላል። ሁኔታው እንዲህ ከሆነ፣ የሰው ሕይወት እንዳያጠፋና የደም ባለዕዳ እንዳይሆን አቅሙ የፈቀደውን ሁሉ ማድረግ ይኖርበታል።—መዝ 51:14፤ በሐምሌ 2017 መጠበቂያ ግንብ ላይ የወጣውን “የአንባቢያን ጥያቄዎች” ተመልከት።

9. የመታሰቢያው በዓል መጋበዣ ዘመቻ ቅዳሜ፣ መጋቢት 2 ይጀምራል

(5 ደቂቃ) በሽማግሌ የሚቀርብ ንግግር። ጉባኤው ከዘመቻው፣ ከልዩ ንግግሩና ከመታሰቢያው በዓል ጋር በተያያዘ ያደረገውን ዝግጅት ግለጽ። አስፋፊዎች በመጋቢትና በሚያዝያ ወራት ለ15 ሰዓት በማገልገል ረዳት አቅኚዎች መሆን እንደሚችሉ አስታውሳቸው።

10. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 6 አን. 9-17

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 40 እና ጸሎት