በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጥር 15-21

ኢዮብ 36–37

ከጥር 15-21

መዝሙር 147 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. አምላክ በሰጠው የዘላለም ሕይወት ተስፋ ላይ መተማመን የምንችለው ለምንድን ነው?

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ራሱ ለዘላለም ይኖራል (ኢዮብ 36:26w15 10/1 13 አን. 1-2)

ይሖዋ ሕይወትን ለማስቀጠል የሚያችል ጥበብም ሆነ ኃይል አለው (ኢዮብ 36:27, 28w20.05 22 አን. 6)

ይሖዋ የዘላለም ሕይወት ማግኘት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ያስተምረናል (ኢዮብ 36:4, 22፤ ዮሐ 17:3)


አምላክ በሰጠው የዘላለም ሕይወት ተስፋ ላይ ጠንካራ እምነት ካለን በሕይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙንን ፈተናዎች በጽናት መቋቋም እንችላለን።—ዕብ 6:19w22.10 28 አን. 16

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ኢዮብ 37:20—በመጽሐፍ ቅዱስ ዘመን ዜና እና መረጃ ብዙውን ጊዜ የሚተላለፈው እንዴት ነበር? (it-1 492)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 5)

6. እምነታችንን ማብራራት

(5 ደቂቃ) ንግግር። ijwfq 57 አን. 5-15—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች በናዚ ዘመን ስደት የደረሰባቸው ለምንድን ነው? (th ጥናት 18)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 49

7. የሕክምና እርዳታ ወይም ቀዶ ጥገና ለሚጠይቁ ሁኔታዎች ተዘጋጁ

(15 ደቂቃ) ውይይት። በሽማግሌ የሚቀርብ።

የይሖዋ ድርጅት፣ አምላክ ከደም ጋር በተያያዘ ያወጣውን ሕግ እንድናከብር የሚረዱ መሣሪያዎችን አዘጋጅቶልናል። (ሥራ 15:28, 29) እነዚህን መሣሪያዎች ጥሩ አድርጋችሁ እየተጠቀማችሁባቸው ነው?

የሕክምና መመሪያ ካርድ (DPA) እና የመታወቂያ ካርድ (ic)፦ እነዚህ ካርዶች ደምን ለሕክምና ከመጠቀም ጋር በተያያዘ ታካሚው ያለውን አቋም የሚገልጹ ናቸው። የተጠመቁ አስፋፊዎች የሕክምና መመሪያ ካርዱን ከጽሑፍ አገልጋዩ ማግኘት ይችላሉ፤ በተጨማሪም ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆቻቸው የመታወቂያ ካርድ መውሰድ ይችላሉ። እነዚህን ካርዶች በማንኛውም ጊዜ ይዘናቸው ልንንቀሳቀስ ይገባል። እነዚህን ካርዶች መሙላት ወይም ማስተካከያ ማድረግ የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ ዛሬ ነገ አትበሉ።

ለነፍሰ ጡር እናቶች የተሰጠ መረጃ (S-401) እና ቀዶ ሕክምና ወይም ኬሞቴራፒ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የተሰጠ መረጃ (S-407)፦ እነዚህ ሰነዶች ለሚደረግልን ሕክምና በተሻለ ሁኔታ ለመዘጋጀት ይረዱናል፤ ይህም ከደም ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን ይጨምራል። ነፍሰ ጡር ከሆናችሁ አሊያም ደግሞ ቀዶ ጥገና ወይም የካንሰር ሕክምና የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ ሽማግሌዎች አስፈላጊውን ሰነድ እንዲሰጧችሁ ጠይቁ።

የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴ (HLC)፦ የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴ አባላት ከደም ጋር ስለተያያዙ ጉዳዮች ለሐኪሞችና ለአስፋፊዎች መረጃ ለመስጠት ዝግጁ የሆኑ ብቃት ያላቸው ሽማግሌዎች ናቸው። ያለደም ሕክምና ማግኘት ስለምትችሉባቸው መንገዶች ሐኪማችሁን ሊያነጋግሩላችሁ ይችላሉ። አስፈላጊ ከሆነ ደግሞ ተባባሪ የሆነ ሐኪም እንድታገኙ ሊረዷችሁ ይችላሉ። በሳምንት 7ቱንም ቀናት በቀን 24 ሰዓት ወንድሞችን ለመርዳት ዝግጁ ናቸው። ሆስፒታል መተኛት፣ ቀዶ ሕክምና ማድረግ ወይም እንደ ካንሰር ሕክምና ያለ ሌላ ሕክምና ማግኘት የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ በተቻለ ፍጥነት የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴውን አነጋግሩ። ሕክምናው ከደም ጋር የተያያዘ ጥያቄ እንደሚያስነሳ ባይሰማችሁም እንኳ እንዲህ ማድረጋችሁ ጠቃሚ ነው። ነፍሰ ጡር የሆኑ እህቶችም እንዲህ ማድረጋቸው አስፈላጊ ነው። እገዛ የሚያስፈልጋችሁ ከሆነ የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴውን አድራሻ እንዲሰጣችሁ አንድን የጉባኤ ሽማግሌ መጠየቅ ትችላላችሁ።

የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴዎች ምን እርዳታ ያበረክታሉ? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

የሕክምና እርዳታ ወይም ቀዶ ጥገና የሚጠይቅ ሁኔታ ካጋጠማችሁ የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴው ሊረዳችሁ የሚችለው እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 67 እና ጸሎት