በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጥር 22-28

ኢዮብ 38–39

ከጥር 22-28

መዝሙር 11 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ተፈጥሮን ለመመልከት ጊዜ ትመድባላችሁ?

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ምድርን ከፈጠረ በኋላ ሥራውን መለስ ብሎ ለመመልከት ጊዜ መድቧል (ዘፍ 1:10, 12፤ ኢዮብ 38:5, 6w21.08 9 አን. 7)

መላእክት ጊዜ ወስደው የይሖዋን የፍጥረት ሥራዎች ተመልክተዋል (ኢዮብ 38:7w20.08 14 አን. 2)

ተፈጥሮን ለመመልከትና ለማድነቅ ጊዜ የምንመድብ ከሆነ በይሖዋ ላይ ያለንን እምነት እናጠናክራለን (ኢዮብ 38:32-35w23.03 17 አን. 8)

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ኢዮብ 38:8-10—ይህ ጥቅስ የይሖዋን ሕግ አውጪነት በተመለከተ ምን ያስተምረናል? (it-2 222)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(2 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ግለሰቡ የመነጋገር ፍላጎት እንደሌለው ስታስተውል ውይይቱን አዎንታዊ በሆነ መንገድ አቁም። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(5 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት ግለሰቡ በቅርቡ የቤተሰቡን አባል በሞት እንዳጣ ነግሮህ ነበር። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 1—ጭብጥ፦ ዛሬ በዓለም ላይ የሚታዩ ክስተቶችና የሰዎች ባሕርይ መበላሸት ለውጥ እየመጣ እንደሆነ ይጠቁማሉ። (th ጥናት 16)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 111

7. ተፈጥሮን መመልከታችን የእይታ አድማሳችንን እንድናሰፋ ይረዳናል

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ኢዮብ ከሦስቱ ጓደኞቹና ከሰይጣን ጥቃት ሲሰነዘርበት በደረሰበት ችግርና በተሰነዘረበት ኢፍትሐዊ የሆነ ትችት ላይ ብቻ ማውጠንጠን ጀመረ።

ኢዮብ 37:14ን አንብብ። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

ኢዮብ መንፈሳዊ ሚዛኑን መልሶ ለማግኘት ምን ማድረግ ነበረበት?

የሚደርስብን ፈተና ከአቅማችን በላይ እንደሆነብን ሲሰማን ተፈጥሮን መመልከታችን የይሖዋን ታላቅነት እንድናስታውስ፣ ለእሱ ያለንን ታማኝነት ለመጠበቅ ያለንን ፍላጎት እንድናጠናክር እንዲሁም እሱ እኛን የመንከባከብ ችሎታ እንዳለው ይበልጥ እንድንተማመን ይረዳናል።—ማቴ 6:26

ከኢዮብ መጽሐፍ የምናገኘው ትምህርት—ከእንስሳት የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

ይህ ቪዲዮ በይሖዋ ላይ ያላችሁን እምነት ያጠናከረላችሁ እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 54 እና ጸሎት