በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጥር 29–የካቲት 4

ኢዮብ 40–42

ከጥር 29–የካቲት 4

መዝሙር 124 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ከኢዮብ ታሪክ የምናገኛቸው ትምህርቶች

(10 ደቂቃ)

የእናንተ እይታ ከይሖዋ እይታ ጋር ሲነጻጸር የተገደበ እንደሆነ አምናችሁ ተቀበሉ (ኢዮብ 42:1-3w10 10/15 3-4 አን. 4-6)

ይሖዋና ድርጅቱ የሚሰጧችሁን ምክር በፈቃደኝነት ተቀበሉ (ኢዮብ 42:5, 6w17.06 25 አን. 12)

ይሖዋ ፈተና ቢያጋጥማቸውም ለእሱ ያላቸውን ታማኝነት የሚጠብቁ ሰዎችን ይባርካል (ኢዮብ 42:10-12፤ ያዕ 5:11w22.06 25 አን. 17-18)

ኢዮብ ንጹሕ አቋሙን በመጠበቁ ይሖዋ ባርኮታል

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ኢዮብ 42:7—የኢዮብ ሦስት ጓደኞች መጥፎ ነገር የተናገሩት በማን ላይ ነው ሊባል ይችላል? ይህን ማወቃችን የሚደርስብንን ፌዝ ለመቋቋም የሚረዳንስ እንዴት ነው? (it-2 808)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ የክርስትና እምነት ተከታይ አይደለም። (lmd ምዕራፍ 5 ነጥብ 3)

5. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

6. ንግግር

(4 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 2—ጭብጥ፦ ምድር ፈጽሞ አትጠፋም። (th ጥናት 13)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 108

7. ሌሎች የይሖዋን ፍቅር እንዲያጣጥሙ እርዷቸው

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ፍቅር የሆነ አምላክ ማምለክ በመቻላችን በጣም ደስተኞች ነን። (1ዮሐ 4:8, 16) ይሖዋ አፍቃሪ አምላክ መሆኑ ወደ እሱ እንድንቀርብ እንዲሁም የእሱ ወዳጆች ሆነን እንድንኖር ያነሳሳናል። የይሖዋ በጎች እንደመሆናችን መጠን ሁላችንም ይሖዋ እንደሚወደን ይሰማናል።

ከቤተሰባችን አባላት፣ ከእምነት አጋሮቻችን እንዲሁም ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት የይሖዋን ፍቅር ለማንጸባረቅ አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ እናደርጋለን። (ኢዮብ 6:14፤ 1ዮሐ 4:11) ፍቅር ማሳየታችን ሌሎች ይሖዋን እንዲያውቁና ወደ እሱ እንዲቀርቡ ሊያነሳሳቸው ይችላል። በአንጻሩ ደግሞ ለሌሎች ፍቅር የማናሳይ ከሆነ የይሖዋን ፍቅር ማጣጣም ሊከብዳቸው ይችላል።

በይሖዋ ቤተሰብ ውስጥ ክርስቲያናዊ ፍቅር አግኝተናል የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

ፍቅር ማሳየት ያለውን አስፈላጊነት በተመለከተ ከሌይ ሌይ እና ከሚሚ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?

የእምነት አጋሮቻችን የይሖዋን ፍቅር እንዲያጣጥሙ መርዳት የምንችለው እንዴት ነው?

  • የይሖዋ ውድ በጎች እንደሆኑ አድርጋችሁ ተመልከቷቸው።—መዝ 100:3

  • በሚያንጽ መንገድ አነጋግሯቸው።—ኤፌ 4:29

  • ስሜታቸውን ለመረዳት ጥረት አድርጉ።—ማቴ 7:11, 12

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

(30 ደቂቃ) bt ምዕ. 5 አን. 1-8በገጽ 39 ላይ ያለው ሣጥን

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 126 እና ጸሎት