በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጥር 8-14

ኢዮብ 34–35

ከጥር 8-14

መዝሙር 30 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ሕይወት ፍትሐዊ እንዳልሆነ ሲሰማን

(10 ደቂቃ)

ይሖዋ ፈጽሞ ፍትሕ የጎደለው ነገር እንደማያደርግ አስታውሱ (ኢዮብ 34:10wp19.1 8 አን. 2)

ክፉዎች ለሚያደርጉት ነገር ተገቢውን ቅጣት እንዳላገኙ ሊሰማን ይችላል፤ ሆኖም ከይሖዋ ሊደበቁ አይችሉም (ኢዮብ 34:21-26w17.04 10 አን. 5)

ኢፍትሐዊ ድርጊት የተፈጸመባቸውን ሰዎች መርዳት የምንችልበት ከሁሉ የተሻለው መንገድ እነሱን ስለ ይሖዋ ማስተማር ነው (ኢዮብ 35:9, 10፤ ማቴ 28:19, 20w21.05 7 አን. 19-20)

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ኢዮብ 35:7—ኤሊሁ “[አምላክ] ከአንተ እጅ ምን ይቀበላል?” ብሎ ኢዮብን ሲጠይቀው ምን ማለቱ ነበር? (w17.04 29 አን. 3)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዝ። (lmd ምዕራፍ 10 ነጥብ 3)

5. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ትናንሽ ልጆች ላሉት ሰው ከ​jw.org ላይ ለወላጆች የሚጠቅም መረጃ ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 4)

6. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 58

7. መደበኛ ባልሆነ መንገድ ‘ቃሉን መስበክ’ ትፈልጋለህ?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ጳውሎስ ጢሞቴዎስን “ቃሉን ስበክ፤ . . . በጥድፊያ ስሜት አገልግል” በማለት አበረታቶታል። (2ጢሞ 4:2) “በጥድፊያ ስሜት” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ አገላለጽ ሁልጊዜ እርምጃ ለመውሰድ ዝግጁ የሆነን በቦታው የተሰየመ ወታደር ወይም ዘብ ለማመልከት ተሠርቶበት ያውቃል። ይህ አገላለጽ፣ ከሰዎች ጋር በምንጨዋወትበት ጊዜ ሁሉ አጋጣሚውን ተጠቅመን ምሥክርነት ለመስጠት ሁልጊዜ ዝግጁ መሆን እንደምንፈልግ ጥሩ አድርጎ ይገልጻል።

ለይሖዋ ያለን ፍቅርና እሱ ላደረገልን መልካም ነገሮች ያለን አድናቆት የእሱን ግሩም ባሕርያት በተመለከተ ለሌሎች እንድንናገር ያነሳሳናል።

መዝሙር 71:8ን አንብብ። ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ጠይቅ፦

የይሖዋን ጥሩነት በተመለከተ የትኞቹን ነገሮች ለሌሎች መናገር ትፈልጋላችሁ?

መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር የሚያነሳሳን ሌላው ነገር ለሰዎች ያለን ፍቅር ነው።

በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እውነትን ሰሙ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  •   መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች እውነትን እንዲሰሙ ያስቻላቸው እንዴት ነው?

  •   የቤተ ክርስቲያን አባል የነበሩት እነዚህ ሰዎች እውነትን መማራቸው የጠቀማቸው እንዴት ነው?

  • ለሰዎች ያለን ፍቅር መደበኛ ባልሆነ መንገድ ለመመሥከር የሚያነሳሳን እንዴት ነው?

  • መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት ሌሎች ስለ ይሖዋ እንዲማሩ ለመርዳት የሚያስችል ውጤታማ መንገድ የሆነው ለምን ይመስላችኋል?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 138 እና ጸሎት