በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከየካቲት 24–መጋቢት 2

ምሳሌ 2

ከየካቲት 24–መጋቢት 2

መዝሙር 35 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. በትጋት የግል ጥናት ማድረግ ያለብን ለምንድን ነው?

(10 ደቂቃ)

ለእውነት ያለንን አድናቆት ለማሳየት (ምሳሌ 2:3, 4w22.08 18 አን. 16)

ጥሩ ውሳኔ ለማድረግ (ምሳሌ 2:5-7w22.10 19 አን. 3-4)

እምነታችንን ለማጠናከር (ምሳሌ 2:11, 12w16.09 23 አን. 2-3)

ራስህን እንዲህ ብለህ ጠይቅ፦ ‘የግል ጥናት ልማዴን ማሻሻል የምችለው እንዴት ነው?’

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • ምሳሌ 2:7—ይሖዋ “ንጹሕ አቋማቸውን ጠብቀው ለሚመላለሱት ጋሻ” የሚሆነው እንዴት ነው? (it-1 1211 አን. 4)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) ከቤት ወደ ቤት። ግለሰቡ ለባለትዳሮች የሚጠቅም መረጃ ከ​jw.org ላይ ማግኘት የሚችለው እንዴት እንደሆነ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 1 ነጥብ 3)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(3 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ባለፈው ውይይታችሁ ወቅት የግለሰቡን ትኩረት ስቦት ስለነበረው ርዕሰ ጉዳይ የሚናገር መጽሔት አበርክት። (lmd ምዕራፍ 9 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) lmd ተጨማሪ መረጃ ሀ ነጥብ 8—ጭብጥ፦ ባልና ሚስት ለትዳራቸው ታማኝ መሆን አለባቸው። (th ጥናት 13)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 96

7. የተሸሸገ ሀብት ማግኘት ትፈልጋላችሁ?

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ወጣቶች፣ የተሸሸገ ሀብት ማግኘት ትፈልጋላችሁ? ከሆነ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በጽንፈ ዓለሙ ውስጥ ካሉት ሀብቶች ሁሉ እጅግ የላቀውን ሀብት ማለትም የአምላክን እውቀት ፈልጋችሁ እንድታገኙ ጋብዟችኋል! (ምሳሌ 2:4, 5) ይህን ሀብት ማግኘት የምትችሉት መጽሐፍ ቅዱስን አዘውትራችሁ ለማንበብ ጊዜ በመመደብና የምታነቡትን ዘገባ በጥልቀት በመመርመር ነው። እንዲህ ካደረጋችሁ ከንባባችሁ ደስታና ጥቅም ታገኛላችሁ።

  • መጽሐፍ ቅዱስን ስታነቡ ራሳችሁን ምን ብላችሁ መጠየቅ ትችላላችሁ? (w24.02 32 አን. 2-3)

  • መልሱን ለማግኘት የትኞቹን መሣሪያዎች መጠቀም ትችላላችሁ?

ከይሖዋ ወዳጆች ተማሩ በሚል ርዕስ የሚወጡት ቪዲዮዎች በምታነቧቸው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ላይ ማሰላሰል የምትችሉት እንዴት እንደሆነ ለመማር ሊረዷችሁ ይችላሉ።

ከይሖዋ ወዳጆች ተማሩ—አቤል የተባለውን ቪዲዮ አጫውት

ዘፍጥረት 4:2-4ን እና ዕብራውያን 11:4ን አንብብ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • አቤል የይሖዋ ወዳጅ መሆኑን ያሳየው እንዴት ነው?

  • አቤል በይሖዋ ላይ እምነት የገነባው እንዴት ነው?

  • እናንተስ እምነታችሁን መገንባት የምትችሉት እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 102 እና ጸሎት