በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጥር 20-26

መዝሙር 138–139

ከጥር 20-26

መዝሙር 93 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. ፍርሃት እንቅፋት እንዲሆንብህ አትፍቀድ

(10 ደቂቃ)

በሙሉ ልባችን ይሖዋን ማወደስ እንፈልጋለን (መዝ 138:1)

በስብሰባ ላይ ሐሳብ መስጠት የሚያስፈራህ ከሆነ በይሖዋ እርዳታ ተማመን (መዝ 138:3)

ፍርሃት የሚሰማህ መሆኑ ስለ አንተ አዎንታዊ ነገር የሚጠቁም ሊሆን ይችላል (መዝ 138:6w19.01 10 አን. 10)

ጠቃሚ ምክር፦ አጭር መልስ መመለሳችን ፍርሃታችንን ለመቀነስ ሊረዳን ይችላል።—w23.04 21 አን. 7

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 139:21, 22—ክርስቲያኖች ሁሉንም ሰው ይቅር ማለት ይጠበቅባቸዋል? (w97 12/1 19 አን. 15)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። (lmd ምዕራፍ 2 ነጥብ 3)

5. ደቀ መዛሙርት ማድረግ

(4 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ግለሰቡ መጽሐፍ ቅዱስን እንዲያጠና ጋብዘው፤ ከዚያም ጥናቱ እንዴት እንደሚካሄድ አሳየው። (lmd ምዕራፍ 10 ነጥብ 3)

6. ንግግር

(5 ደቂቃ) ijwyp ርዕስ 105—ጭብጥ፦ ዓይናፋርነትን ማሸነፍ የምችለው እንዴት ነው? (th ጥናት 16)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 59

7. ዓይናፋር ብትሆኑም በአገልግሎታችሁ ውጤታማ መሆን ትችላላችሁ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ዓይናፋር እንደሆንክ ይሰማሃል? የሰው ዓይን ውስጥ ባትገባ ደስ ይልሃል? ሌሎችን ስለማነጋገር ስታስብ ጭንቅ ይልሃል? አንዳንድ ጊዜ፣ ዓይናፋር መሆናችን ማድረግ የምንፈልገውን ነገር እንዳናደርግ እንቅፋት ሊሆንብን ይችላል። ይሁንና ከዓይናፋርነት ጋር የሚታገሉ በርካታ ክርስቲያኖች አገልግሎታቸውን ማስፋት አልፎ ተርፎም ውጤታማ መሆን ችለዋል። ከእነሱ ምሳሌ ምን ትምህርት እናገኛለን?

ዓይናፋር ብሆንም ምርጤን መስጠት ችያለሁ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • እህት ሊ ‘ጉልበቷን ይሖዋን ለማገልገል እንድትጠቀምበት’ አያቷ የሰጠቻትን ምክር በሥራ ላይ በማዋሏ ምን ጥቅም አግኝታለች?

ሙሴ፣ ኤርምያስና ጢሞቴዎስ የዓይናፋርነት ችግር ሊኖርባቸው እንደሚችል መጽሐፍ ቅዱስ ይጠቁማል። (ዘፀ 3:11፤ 4:10፤ ኤር 1:6-8፤ 1ጢሞ 4:12) ያም ቢሆን ይሖዋ ከጎናቸው ስለነበር በእሱ አገልግሎት አስደናቂ ነገሮችን ማከናወን ችለዋል። (ዘፀ 4:12፤ ኤር 20:11፤ 2ጢሞ 1:6-8)

ኢሳይያስ 43:1, 2ን አንብብ። ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ምን ቃል ገብቶላቸዋል?

ይሖዋ በዛሬው ጊዜ ዓይናፋር የሆኑ ሰዎች በአገልግሎታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚረዳቸው እንዴት ነው?

መጠመቃችሁ ይበልጥ ደስተኛ እንድትሆኑ የሚረዳችሁ እንዴት ነው?—ተቀንጭቦ የተወሰደ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • እህት ጃክሰን በአገልግሎቷ የይሖዋን ኃይልና ድጋፍ ያየችው እንዴት ነው?

  • አገልግሎት ዓይናፋር የሆኑ ሰዎችን የሚረዳቸው እንዴት ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 151 እና ጸሎት