በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከጥር 27–የካቲት 2

መዝሙር 140–143

ከጥር 27–የካቲት 2

መዝሙር 44 እና ጸሎት | የመግቢያ ሐሳብ (1 ደቂቃ)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

1. እርዳታ ለማግኘት ካቀረባችሁት ልመና ጋር የሚስማማ እርምጃ ውሰዱ

(10 ደቂቃ)

ምክርና እርማት ለመቀበል ፈቃደኞች ሁኑ (መዝ 141:5w22.02 12 አን. 13-14)

በይሖዋ የማዳን ሥራዎች ላይ አሰላስሉ (መዝ 143:5w10 3/15 32 አን. 4)

የይሖዋ ዓይነት አመለካከት ለማዳበር ጥረት አድርጉ (መዝ 143:10w15 3/15 32 አን. 2)

ከመዝሙር 140–143 ዳዊት እርዳታ ለማግኘት ያቀረበውን ልመና ብቻ ሳይሆን ከልመናው ጋር የሚስማማ እርምጃ እንደወሰደ የሚያሳዩ ሐሳቦችንም ይዟል።

2. መንፈሳዊ ዕንቁዎች

(10 ደቂቃ)

  • መዝ 140:3—ዳዊት የክፉ ሰዎችን ምላስ ከእባብ ምላስ ጋር ያመሳሰለው ለምንድን ነው? (it-2 1151)

  • ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?

3. የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

4. ውይይት መጀመር

(4 ደቂቃ) መደበኛ ያልሆነ ምሥክርነት። ለግለሰቡ ተግባራዊ እርዳታ ከሰጠህ በኋላ ውይይት ጀምር። (lmd ምዕራፍ 3 ነጥብ 5)

5. ተመላልሶ መጠየቅ

(3 ደቂቃ) የአደባባይ ምሥክርነት። ግለሰቡ ሥራ እንደሚበዛበት ይነግርሃል። (lmd ምዕራፍ 7 ነጥብ 3)

6. እምነታችንን ማብራራት

(5 ደቂቃ) ሠርቶ ማሳያ። ijwfq ርዕስ 21—ጭብጥ፦ የይሖዋ ምሥክሮች ደም የማይወስዱት ለምንድን ነው? (th ጥናት 7)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መዝሙር 141

7. የሕክምና እርዳታ ወይም ቀዶ ጥገና ለሚጠይቁ ሁኔታዎች ተዘጋጁ

(15 ደቂቃ) ውይይት።

ይሖዋ “በጭንቅ ጊዜ ፈጥኖ የሚደርስልን ረዳታችን” እንደሚሆን ቃል ገብቶልናል። (መዝ 46:1) የሕክምና እርዳታ ወይም ቀዶ ጥገና የሚጠይቁ ሁኔታዎች ጭንቀት ሊፈጥሩ ይችላሉ። ይሁንና ይሖዋ እንዲህ ላሉ ሁኔታዎች ለመዘጋጀት የሚያስፈልገንን ነገር በሙሉ አዘጋጅቶልናል። ለምሳሌ ድርጅቱ የሕክምና መመሪያ ካርድ (DPA)፣ የመታወቂያ ካርድ a እና የሕክምና መረጃ የሚሰጡ ሌሎች ሰነዶችን b እንዲሁም የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴዎችን አዘጋጅቶልናል። እነዚህ ዝግጅቶች ይሖዋ ከደም ጋር በተያያዘ ያወጣውን ሕግ እንድናከብር ይረዱናል።—ሥራ 15:28, 29

የሕክምና እርዳታ ለሚጠይቁ ሁኔታዎች ተዘጋጅታችኋል? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦

  • አንዳንዶች የሕክምና መመሪያ ካርድ መሙላታቸው የጠቀማቸው እንዴት ነው?

  • ለነፍሰ ጡር እናቶች የተሰጠ መረጃ (S-401) የሚለው ሰነድ አንዳንዶችን የረዳቸው እንዴት ነው?

  • ሆስፒታል መተኛት፣ ቀዶ ሕክምና ማድረግ ወይም እንደ ካንሰር ሕክምና ያለ ሌላ ሕክምና ማግኘት የሚያስፈልገን ከሆነ ሕክምናው ከደም ጋር የተያያዘ ጥያቄ እንደሚያስነሳ ባይሰማንም እንኳ በተቻለ ፍጥነት የሆስፒታል አገናኝ ኮሚቴውን ማነጋገራችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?

8. የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት

የመደምደሚያ ሐሳብ (3 ደቂቃ) | መዝሙር 103 እና ጸሎት

a የተጠመቁ አስፋፊዎች የሕክምና መመሪያ ካርዱን ከጽሑፍ አገልጋዩ ማግኘት ይችላሉ፤ በተጨማሪም ለአካለ መጠን ላልደረሱ ልጆቻቸው የመታወቂያ ካርድ መውሰድ ይችላሉ።

b ለነፍሰ ጡር እናቶች የተሰጠ መረጃ (S-401)፣ ቀዶ ሕክምና ወይም ኬሞቴራፒ ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች የተሰጠ መረጃ (S-407) እንዲሁም የሕክምና እርዳታ የሚያስፈልገው ልጅ ላላቸው ወላጆች የተዘጋጀ መረጃ (S-55) የተባሉት ሰነዶች ሲያስፈልጓችሁ ሽማግሌዎቻችሁን መጠየቅ ትችላላችሁ።