የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ጥር 2016
የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! መጽሔቶችን እንዲሁም ከአምላክ የተላከ ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ለማበርከት የሚረዱ ሐሳቦች።
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
እውነተኛው አምልኮ ተግቶ መሥራት ይጠይቃል
ንጉሥ ሕዝቅያስ እውነተኛውን መልሶ ለማቋቋም የወሰደውን ቆራጥ እርምጃ በዓይነ ሕሊናህ ለማየት ሞክር። በዚህ ረገድ እንዲረዳህ ሥዕላዊ መግለጫውን፣ ካርታውንና በሁለተኛ ዜና ከ29-30 ላይ የተጠቀሱትን ክንውኖች የሚገልጸውን የጊዜ ሰሌዳ ተጠቀም።
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ ጥናት መምራት የሚቻለው እንዴት ነው?
ከአምላክ የተላከ ምሥራች! በተባለው ብሮሹር አማካኝነት ውጤታማ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለመምራት የሚረዱ አምስት ቀላል መንገዶች።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
እውነተኛ አምልኮ የሚካሄድባቸውን ቦታዎች መገንባትና በጥሩ ሁኔታ መያዝ
በአምልኮ ቦታዎቻችን ለቅዱስ አገልግሎት ቅንዓትና ፍቅር እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ይሖዋ ለእውነተኛ ንስሐ ከፍ ያለ ግምት ይሰጣል
ንጉሥ ምናሴ ልባዊ ንስሐ መግባቱ ጥሩ ውጤት አስገኝቷል። በግዞት ከመወሰዱ በፊትና ከባቢሎን ምርኮ ከተመለሰ በኋላ ያደረጋቸውን ነገሮች አወዳድር። (2 ዜና 33-36)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ይሖዋ ቃሉን ይጠብቃል
ዕዝራ 1-5 ላይ የተገለጹት ክንውኖች የተፈጸሙባቸው ዘመናት። ከባቢሎን የተመለሱት አይሁዳውያን ብዙ እንቅፋቶች ቢያጋጥሟቸውም ቤተ መቅደሱን መልሰው በመገንባት እውነተኛውን አምልኮ ዳግመኛ አቋቁመዋል።
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ይሖዋ ራሳቸውን በፈቃደኝነት የሚያቀርቡ አገልጋዮች ይፈልጋል
ዕዝራና ከእሱ ጋር ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት ሰዎች ጠንካራ እምነት ማሳየት፣ ለእውነተኛው አምልኮ መቅናትና ደፋሮች መሆን አስፈልጓቸዋል። ሥዕሉንና ካርታውን ተጠቅመህ ያደረጉትን ጉዞ በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት መጣል
ለመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ፍላጎት ላሳዩ ሰዎች ውጤታማ ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ የሚረዱ ሦስት እርምጃዎች።