በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ጥር 18-24

ዕዝራ 1-5

ጥር 18-24
  • መዝሙር 85 እና ጸሎት

  • የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

  • ይሖዋ ቃሉን ይጠብቃል”፦ (10 ደቂቃ) [የዕዝራ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]

  • መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)

    • ዕዝራ 1:3-6—ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ፈቃደኛ ያልሆኑት እስራኤላውያን እንዲህ ያላደረጉት እምነት ስላነሳቸው ላይሆን ይችላል የምንለው ለምንድን ነው? (w06 1/15 17 አን. 5፤ 19 አን. 1)

    • ዕዝራ 4:1-3—ታማኝ የሆኑት የአምላክ አገልጋዮች የቀረበላቸውን ግብዣ ያልተቀበሉት ለምንድን ነው? (w06 1/15 19 አን. 3)

    • የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?

    • የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ ዕዝራ 3:10–4:7 (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

  • መመሥከር፦ (2 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በቅርብ በደረሳችሁ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የጀርባ ገጽ ላይ የሚገኘውን ርዕስ አስተዋውቅ። ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።

  • ተመላልሶ መጠየቅ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በቅርቡ በደረሳችሁ የመጠበቂያ ግንብ መጽሔት የጀርባ ገጽ ላይ የሚገኘውን ርዕስ ስታስተዋውቅ በጎ ምላሽ ሰጥቶ ለነበረ ሰው እንዴት ተመላልሶ መጠየቅ ማድረግ እንደሚቻል አሳይ። ለቀጣዩ ተመላልሶ መጠየቅ መሠረት ጣል።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት እንዴት እንደሚመራ አሳይ። (bh 20-21 አን. 6-8)

ክርስቲያናዊ ሕይወት

  • መዝሙር 40

  • ‘እነዚህ ነገሮች ሁሉ ይሰጧችኋል’፦ (5 ደቂቃ) በማቴዎስ 6:33 እና በሉቃስ 12:22-24 ላይ ተመሥርቶ የሚቀርብ ንግግር። አስፋፊዎች መንግሥቱን ሲያስቀድሙ ይሖዋ የሚያስፈልጓቸውን ቁሳዊ ነገሮች በማሟላት ቃሉን የጠበቀው እንዴት እንደሆነ የሚያሳዩ ተሞክሮዎችን እንዲናገሩ ጋብዝ።

  • ቃላችሁ “አዎ ሆኖ እያለ አይደለም” ነው?፦ (10 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። (w14 3/15 30-32)

  • የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ ia ምዕ. 2 አን. 13-23 እና የምዕራፉ ክለሳ (30 ደቂቃ)

  • ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)

  • መዝሙር 41 እና ጸሎት