በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት መጣል

በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ለተመላልሶ መጠየቅ መሠረት መጣል

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

የዘራነውን የእውነት ዘር ውኃ ማጠጣት ይኖርብናል። (1ቆሮ 3:6) ፍላጎት ያለው ሰው ስናገኝ በቀጣዩ ጊዜ ውይይት ልናደርግበት የምንችል አንድ ጥያቄ ማንሳታችን ጠቃሚ ነው። ይህም ግለሰቡ ጉጉት እንዲያድርበት የሚያደርግ ከመሆኑም ሌላ ለተመላልሶ መጠየቅ በቀላሉ ዝግጅት እንድናደርግ ይረዳናል። ተመልሰን ስንሄድ የመጣነው ባለፈው ጊዜ ላነሳነው ጥያቄ መልስ ልንሰጠው እንደሆነ ልንገልጽለት እንችላለን።

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ከቤት ወደ ቤት ለማገልገል መግቢያ ስትዘጋጁ በቀጣዩ ጊዜ መልስ ልትሰጡበት የምትችሉትን ጥያቄም ማዘጋጀት እንዳለባችሁ አስታውሱ። ጥያቄው በምታበረክቱት ጽሑፍ ላይ መልስ የተሰጠበት ሊሆን ይችላል። ወይም ደግሞ ተመላልሶ መጠየቅ በምታደርጉበት ወቅት ልታበረክቱት ባሰባችሁት የማስጠኛ ጽሑፍ ላይ መልስ የተሰጠበት ሊሆን ይችላል።

  • ፍላጎት ካሳየው ሰው ጋር የምታደርጉትን ውይይት ስታጠናቅቁ ተመልሳችሁ በመምጣት ልታነጋግሩት እንደምትፈልጉ ከገለጻችሁለት በኋላ ያዘጋጃችሁትን ጥያቄ አንሱ። ከተቻለ አድራሻውን ተቀበሉት።

  • ቀጠሮ ከያዛችሁ ሰዓት አክብሩ።—ማቴ 5:37