በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዕዝራ 6-10

ይሖዋ ራሳቸውን በፈቃደኝነት የሚያቀርቡ አገልጋዮች ይፈልጋል

ይሖዋ ራሳቸውን በፈቃደኝነት የሚያቀርቡ አገልጋዮች ይፈልጋል

ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም ለመመለስ ተዘጋጀ

7:6, 22፤ 8:26, 27

  • ዕዝራ ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ በዚያ የይሖዋን አምልኮ ማስፋፋት እንዲችል ንጉሥ አርጤክስስ ፈቃድ ሰጠው

  • ንጉሡ ዕዝራ “የጠየቀውን ሁሉ ሰጠው”፤ ለይሖዋ ቤት የሚሆን ወርቅ፣ ብር፣ ስንዴ፣ ወይን ጠጅ፣ ዘይትና ጨው የሰጠው ሲሆን የተሰጡት ነገሮች ዛሬ ባለው ዋጋ ሲሰሉ ከ100,000,000 የአሜሪካ ዶላር በላይ ያወጣሉ

ዕዝራ፣ ይሖዋ ለአገልጋዮቹ ጥበቃ እንደሚያደርግ ሙሉ እምነት ነበረው

7:13፤ 8:21-23

  • ወደ ኢየሩሳሌም መመለስ አስቸጋሪ ነበር

  • አደገኛ በሆነ ክልል 1,600 ኪሎ ሜትር ገደማ እንደተጓዙ ይገመታል

  • ጉዞው 4 ወር ገደማ ፈጅቷል

  • ወደ ኢየሩሳሌም የተመለሱት ሰዎች ጠንካራ እምነት ማሳየት፣ ለእውነተኛው አምልኮ መቅናትና ደፋሮች መሆን አስፈልጓቸዋል

ዕዝራ የተጓዘው . . .

ከ25,650 ኪሎ ግራም በላይ ወይም ከ3 ትላልቅ የአፍሪካ ዝሆኖች ክብደት ጋር የሚመጣጠን ወርቅና ብር ይዞ ነበር!

ተመላሾቹ ያጋጠሟቸው ተፈታታኝ ሁኔታዎች፦

ወራሪ ቡድኖች፣ በረሃ እና አደገኛ የዱር አራዊት