በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ምሥራች የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ ጥናት መምራት የሚቻለው እንዴት ነው?
-
ግለሰቡ በዋናው ነጥብ ላይ እንዲያተኩር ለመርዳት ደመቅ ተደርጎ የተጻፈውን ጥያቄ አንብብ።
-
ከጥያቄው ቀጥሎ ያለውን አንቀጽ አንብብ።
-
በሰያፍ የተጻፉትን ጥቅሶች አንብብ፤ ግለሰቡ እነዚህ ጥቅሶች ለአንቀጹ ጥያቄ መልስ የሚሰጡት እንዴት እንደሆነ መገንዘብ እንዲችል ለመርዳት ቀለል ያሉ ጥያቄዎችን ተጠቀም።
-
በጥያቄው ሥር ተጨማሪ አንቀጽ ካለ ሁለተኛውና ሦስተኛው ነጥብ ላይ የተገለጸውን ሐሳብ በድጋሚ በመጠቀም ግለሰቡን አወያየው። jw.org ላይ የወጣ ከጥያቄው ጋር የሚሄድ ቪዲዮ ካለ በውይይታችሁ መካከል ቪዲዮውን አሳየው።
-
ግለሰቡ ዋናውን ነጥብ መረዳት አለመረዳቱን ለማረጋገጥ ለአንቀጹ የቀረበውን ጥያቄ ጠይቀው።