በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአቀራረብ ናሙናዎች

የአቀራረብ ናሙናዎች

መጠበቂያ ግንብ

ጥያቄ፦ ሁሉም ሰው ይህን ሐሳብ ተግባራዊ ቢያደርግ ዓለም የተሻለች ቦታ የምትሆን አይመስልዎትም?

ጥቅስ፦ ዕብ 13:18

አበርክት፦ መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም ነገር ሐቀኞች እንድንሆን ያበረታታናል። በሁሉም የሕይወታችን ዘርፍ ሐቀኛ መሆን ይጠበቅብናል። ይህ መጠበቂያ ግንብ የሚናገረው ስለዚህ ጉዳይ ነው።

መጠበቂያ ግንብ (የጀርባ ገጽ)

ጥያቄ፦ እስቲ አንድ ጥያቄ ልጠይቅዎት። [የመጀመሪያውን ጥያቄ አንብብ።] ስንሞት ሌላ አካል ይዘን መኖራችንን እንደምንቀጥል የሚያምኑ ሰዎች አሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሞት የሁሉ ነገር መጨረሻ እንደሆነ ይሰማቸዋል። እርስዎስ ምን ይላሉ?

ጥቅስ፦ መክብብ 9:5

አበርክት፦ ይህ ርዕስ መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ጉዳይ በተመለከተ ምን እንደሚል ያብራራል። መጽሔቱን ወስደው ያንብቡትና ሌላ ጊዜ መጥቼ ልንወያይበት እንችላለን።

ከአምላክ የተላከ ምሥራች!

አበርክት፦ የመጣሁት በነፃ ስለምንሰጠው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ልነግርዎት ነው። ይህ ብሮሹር ወሳኝ ለሆኑ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስዎ ላይ እንዴት መልስ ማግኘት እንደሚችሉ ይገልጻል።

ጥያቄ፦ መጽሐፍ ቅዱስን አንብበው ያውቃሉ? ይህ ብሮሹር መጽሐፍ ቅዱስን ቀላል በሆነ መንገድ እንዴት እንደሚያስተምር ላሳይዎት። [በትምህርት 2 ጥያቄ 1 ላይ ተወያዩ።]

ጥቅስ፦ ራእይ 4:11

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።