ክርስቲያናዊ ሕይወት
በስደት ላይ ለሚገኙ ክርስቲያኖች መጸለያችሁን አትርሱ
ሰይጣን አገልግሎታችንን ለማደናቀፍ ሲል ስደት እንደሚያስነሳ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ አስቀድሞ ተነግሯል። (ዮሐ 15:20፤ ራእይ 12:17) በሌሎች አገሮች የሚገኙ ስደት የሚደርስባቸውን የእምነት ባልንጀሮቻችንን እንዴት ልንረዳቸው እንችላለን? ልንጸልይላቸው እንችላለን። “ጻድቅ ሰው የሚያቀርበው ምልጃ ታላቅ ኃይል አለው።”—ያዕ 5:16
ስለ ምን መጸለይ እንችላለን? ይሖዋ ለወንድሞቻችንና ለእህቶቻችን ድፍረት እንዲሰጣቸው ልንጸልይ እንችላለን። (ኢሳ 41:10-13) እንዲሁም “በጸጥታና በተረጋጋ ሁኔታ መኖራችንን” እንድንቀጥል ባለሥልጣናት ለስብከት ሥራችን አዎንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው መጸለይ እንችላለን። —1ጢሞ 2:1, 2
ጳውሎስና ጴጥሮስ ስደት በደረሰባቸው ወቅት፣ የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች ስማቸውን ጠቅሰው ጸልየውላቸው ነበር። (ሥራ 12:5፤ ሮም 15:30, 31) በዛሬው ጊዜ ስደት እየደረሰባቸው ያሉትን ወንድሞች ሁሉ በስም ባናውቃቸውም ጉባኤያቸውን፣ አገራቸውን ወይም አካባቢያቸውን ጠቅሰን ስለ እነሱ መጸለይ እንችላለን።