በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ማቴዎስ 1-3

‘መንግሥተ ሰማያት ቀርቧል’

‘መንግሥተ ሰማያት ቀርቧል’

3:4

  • የዮሐንስ አለባበስና ውጫዊ ገጽታ፣ ሙሉ በሙሉ የአምላክን ፈቃድ በማድረግ ላይ ያተኮረ ቀላል ሕይወት እንደሚመራ በግልጽ የሚያሳይ ነበር

  • ዮሐንስ የኢየሱስ መንገድ ጠራጊ በመሆን ያገኘው ልዩ መብት ከከፈለው ከማንኛውም መሥዋዕትነት የበለጠ ዋጋ አለው

ኑሯችንን ቀላል ማድረጋችን በይሖዋ አገልግሎት ተጨማሪ አስተዋጽኦ እንድናበረክት የሚያስችለን ከመሆኑም ሌላ ከፍተኛ እርካታ ያስገኝልናል። ኑሯችሁን ቀላል ለማድረግ የሚከተሉትን እርምጃዎች መውሰድ ትችላላችሁ፦

  • የሚያስፈልጓችሁን ነገሮች ብቻ ለዩ

  • አላስፈላጊ ወጪዎችን ቀንሱ

  • አቅማችሁን ያገናዘበ ባጀት አውጡ

  • የማትጠቀሙባቸውን ዕቃዎች አስወግዱ

  • ያለባችሁን ዕዳ ሁሉ ክፈሉ

  • ሰብዓዊ ሥራ የምትሠሩበትን ሰዓት ቀንሱ

የዮሐንስ ምግብ አንበጣና የዱር ማር ነበር

ኑሮዬን ቀላል ማድረጌ የትኛው ግቤ ላይ እንድደርስ ይረዳኛል?