ከጥር 22-28
ማቴዎስ 8-9
መዝሙር 17 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ኢየሱስ ሰዎችን ይወድ ነበር”፦ (10 ደቂቃ)
ማቴ 8:1-3—ኢየሱስ በሥጋ ደዌ ለተያዘው ሰው ለየት ያለ ርኅራኄ አሳይቶታል (“ዳሰሰው፣” “እፈልጋለሁ” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች—ማቴ 8:3፣ nwtsty)
ማቴ 9:9-13—ኢየሱስ ሌሎች ይንቋቸው ለነበሩ ሰዎች ፍቅር አሳይቷል (“እየበላ፣” “ቀረጥ ሰብሳቢዎች” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች—ማቴ 9:10፣ nwtsty)
ማቴ 9:35-38—ኢየሱስ ለሰዎች የነበረው ፍቅር ደክሞት በነበረ ጊዜም እንኳ ምሥራቹን እንዲሰብክና ተጨማሪ ሠራተኞችን እንዲልክ ወደ አምላክ እንዲጸልይ አነሳስቶታል (“አዘነላቸው” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማቴ 9:36፣ nwtsty)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ማቴ 8:8-10—ኢየሱስ ከጦር መኮንኑ ጋር ካደረገው ውይይት ምን እንማራለን? (w02 8/15 13 አን. 16)
ማቴ 9:16, 17—ኢየሱስ በእነዚህ ሁለት ምሳሌዎች ላይ ሊያስተላልፍ የፈለገው ነጥብ ምንድን ነው? (jy ገጽ 70 አን. 6)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ማቴ 8:1-17
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) በውይይት ናሙናው ጀምር። ግለሰቡ በስብሰባ ላይ እንዲገኝ ጋብዝ።
ሦስተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመረጥከውን ጥቅስ ተጠቀም፤ ከዚያም አንድ የማስጠኛ ጽሑፍ አበርክት።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bhs ገጽ 47 አን. 18-19
ክርስቲያናዊ ሕይወት
‘በእርግጥም አምላክ ኢየሱስን ጌታም ክርስቶስም አደረገው’—ክፍል 1፣ ተቀንጭቦ የተወሰደ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። ማቴዎስ 9:18-25ን ካነበብክ በኋላ ተቀንጭቦ የተወሰደውን ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ጠይቅ፦
ኢየሱስ ለታመመችው ሴትና ለኢያኢሮስ አሳቢነት ያሳየው እንዴት ነው?
ይህ ዘገባ በመንግሥቱ አገዛዝ ሥር የሚኖረውን ሕይወት አስመልክቶ ስለሚናገሩት የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ምን ስሜት እንዲያድርብህ ያደርጋል?
ኢየሱስ ለሰዎች ፍቅር በማሳየት ረገድ የተወዉን ምሳሌ መከተል የምንችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) kr ምዕ. 21 አን. 15-20፤ “በቅርቡ የሚፈጸሙ ክንውኖች” የሚለው ሣጥን እና “የአምላክ መንግሥት ለአንተ ምን ያህል እውን ነው?” የሚለው የክለሳ ሣጥን
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 149 እና ጸሎት