ኢየሱስ ሰዎችን ይወድ ነበር
ማቴዎስ ምዕራፍ 8 እና 9 ኢየሱስ በገሊላ ግዛት ውስጥ ስላከናወነው አገልግሎት ይናገራል። ኢየሱስ ሰዎችን በመፈወስ ከፍተኛ ኃይል እንዳለው አሳይቷል፤ ከምንም በላይ ግን ይህ ድርጊቱ ለሰው ልጆች ያለውን ታላቅ ፍቅርና ርኅራኄ የሚያሳይ ነው።
-
ኢየሱስ በሥጋ ደዌ የተያዘን ሰው ፈውሷል።—ማቴ 8:1-3
-
ኢየሱስ የአንድን የጦር መኮንን አገልጋይ ፈውሷል።—ማቴ 8:5-13
የጴጥሮስን አማት ፈውሷል።—ማቴ 8:14, 15
አጋንንትን ያስወጣ ከመሆኑም ሌላ ሥቃይ ላይ የነበሩ ሰዎችን ፈውሷል።—ማቴ 8:16, 17
-
ኢየሱስ ለየት ያለ ኃይል ያላቸውን አጋንንት በማስወጣት የአሳማ መንጋ ውስጥ እንዲገቡ አድርጓል።—ማቴ 8:28-32
-
ኢየሱስ ሽባ የነበረን ሰው ፈውሷል።—ማቴ 9:1-8
ልብሱን የነካችን አንዲት ሴት ፈውሷል እንዲሁም የኢያኢሮስን ሴት ልጅ ከሞት አስነስቷል።—ማቴ 9:18-26
ዓይነ ስውርና ዱዳ የነበሩ ሰዎችን ፈውሷል።—ማቴ 9:27-34
-
ኢየሱስ ማንኛውንም ዓይነት በሽታና ማንኛውንም ዓይነት ሕመም እየፈወሰ በየከተማውና በየመንደሩ ይዞር ነበር።—ማቴ 9:35, 36
ለማገኛቸው ሰዎች ፍቅርና ርኅራኄ እንዳለኝ ማሳየት የምችልባቸው ምን ተጨማሪ መንገዶች አሉ?