ከጥር 29–የካቲት 4
ማቴዎስ 10-11
መዝሙር 4 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“ኢየሱስ የእረፍት ምንጭ ነበር”፦ (10 ደቂቃ)
ማቴ 10:29, 30—ይሖዋ ስለ እያንዳንዳችን እንደሚያስብ ኢየሱስ የሰጠው ማረጋገጫ እረፍት ይሰጣል (“ድንቢጦች፣” “አነስተኛ ዋጋ ባላት ሳንቲም፣” “የራሳችሁ ፀጉር እንኳ አንድ ሳይቀር ተቆጥሯል” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች እና “ድንቢጥ” ሚዲያ—ማቴ 10:29, 30፣ nwtsty)
ማቴ 11:28—ይሖዋን ማገልገል እረፍት ይሰጣል (“ሸክም የከበዳችሁ፣” “እረፍት እሰጣችኋለሁ” ለጥናት የሚረዱ መረጃዎች—ማቴ 11:28፣ nwtsty)
ማቴ 11:29, 30—ለክርስቶስ ሥልጣንና አመራር መገዛት እረፍት ያስገኛል (“ቀንበሬን ተሸከሙ” ለጥናት የሚረዳ መረጃ—ማቴ 11:29፣ nwtsty)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ማቴ 11:2, 3—መጥምቁ ዮሐንስ ይህን ጥያቄ የጠየቀው ለምንድን ነው? (jy ገጽ 96 አን. 2-3)
ማቴ 11:16-19—እነዚህን ጥቅሶች መረዳት ያለብን እንዴት ነው? (jy ገጽ 98 አን. 1-2)
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ትምህርት አግኝታችኋል?
ከዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ምን ሌሎች መንፈሳዊ ዕንቁዎች አግኝታችኋል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ማቴ 11:1-19
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
ሁለተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የውይይት ናሙናዎቹን ተመልከት።
ሦስተኛው ተመላልሶ መጠየቅ፦ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) የመረጥከውን ጥቅስና ለቀጣዩ ተመላልሶ መጠየቅ ያዘጋጀኸውን ጥያቄ ተጠቀም።
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (6 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) bhs ገጽ 45-46 አን. 15-16—ግለሰቡ በስብሰባ ላይ እንዲገኝ ጋብዝ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
‘የደከማቸውንና ሸክም የከበዳቸውን ሁሉ’ ማጽናናት፦ (15 ደቂቃ) ቪዲዮውን አጫውት። ከዚያም በሚከተሉት ጥያቄዎች ላይ ተወያዩ፦
አንዳንዶች ማጽናኛ እንዲፈልጉ የሚያደርግ ምን ሁኔታ አጋጥሟቸዋል?
ይሖዋና ኢየሱስ በድርጅቱ በኩል እነዚህን ሰዎች እረፍት እንዲያገኙ የረዷቸው እንዴት ነው?
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች የእረፍት ምንጭ የሆኑት እንዴት ነው?
እያንዳንዳችን ለሌሎች የእረፍት ምንጭ መሆን የምንችለው እንዴት ነው?
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) kr ምዕ. 22 አን. 1-7
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 142 እና ጸሎት