ኢየሱስ የእረፍት ምንጭ ነበር
“ቀንበሬ ልዝብ [ነው]”
ኢየሱስ አናጺ የነበረ እንደመሆኑ መጠን ቀንበር * የሚሠራው እንዴት እንደሆነና ቀንበሩ የማይጎዳ እንዲሆን ሲባል በጨርቅ ወይም በቆዳ ይሸፈን እንደነበር ያውቃል። በተጠመቅንበት ጊዜ የኢየሱስ ደቀ መዝሙር መሆን የሚያስከትለውን ቀንበር ተሸክመናል፤ ይህም ከባድ ሥራ እንድንሠራና ትልቅ ኃላፊነት እንድንሸከም የሚያደርግ እርምጃ ነው። ይሁንና እንዲህ ማድረጋችን እረፍት እንድናገኝ እንዲሁም ብዙ በረከት እንድናጭድ አስችሎናል።
በኢየሱስ ቀንበር ሥር ከሆናችሁበት ጊዜ ጀምሮ ምን በረከቶች አግኝታችኋል?
^ አን.5 “ቀንበር” ተብሎ የተተረጎመው ቃል መጀመሪያ ላይ በተጻፈበት ቋንቋ ሰዎች በሁለት በኩል ዕቃ ለመሸከም ሲሉ ትከሻቸው ላይ የሚያደርጉትን እንጨትም ሊያመለክት ይችላል።