ሰዎች በስብሰባ ላይ እንዲገኙ ሲጋብዙ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ጥቅምት 2016

የአቀራረብ ናሙናዎች

ለንቁ! መጽሔት፣ ለጉባኤ ስብሰባ መጋበዣና ስንሞት ምን እንደምንሆን ለሚገልጸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውነት የተዘጋጁ የአቀራረብ ናሙናዎች። ናሙናዎቹን ተጠቅመህ የራስህን የአቀራረብ ናሙና አዘጋጅ።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን”

ይሖዋ በእሱ ላይ እምነት ስንጥል እንደሚክሰን በምሳሌ ምዕራፍ 3 ላይ ማረጋገጫ እናገኛለን። በሙሉ ልብህ በይሖዋ የምትታመን መሆን አለመሆንህን ማወቅ የምትችለው እንዴት ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“ልባችሁን . . . አታዘንብሉ”

ምሳሌ ምዕራፍ 7 የይሖዋን መመሪያዎች ከመጠበቅ ዞር እንዲል ልቡ እንዲያታልለው ስለፈቀደ አንድ ወጣት ይገልጻል። ይህ ወጣት ከሠራቸው ስህተቶች ምን ትምህርት እናገኛለን?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ጥበብ ከወርቅ የተሻለ ነው

ምሳሌ 16 ጥበብ ማግኘት ወርቅ ከማግኘት እንደሚበልጥ ይናገራል። ጥበብ ይህን ያህል አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው?

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ጥሩ መልስ መስጠት የሚቻለው እንዴት ነው?

አንድ ሰው ጥሩ መልስ ሲሰጥ ራሱንም ሆነ ጉባኤውን ይጠቅማል። ጥሩ መልስ የሚባለው ምን ዓይነት መልስ ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ከሌሎች ጋር በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ

በይሖዋ ሕዝቦች መካከል ያለው ሰላም የተገኘው እንዲሁ በአጋጣሚ አይደለም። በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን ምክር መከተል ስሜትን ለመቆጣጠርና ሰላም ለማስፈን ይረዳናል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“ልጅን ሊሄድበት በሚገባው መንገድ አሠልጥነው”

ልጆችን በተገቢው መንገድ ለማሠልጠን ተግሣጽ አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ምሳሌ 22 ለወላጆች የሚጠቅም ግሩም ምክር ይዟል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የJW.ORG አድራሻ ካርድን በሚገባ እየተጠቀማችሁበት ነው?

ሰዎች ወደ አምላክ ቃልና ወደ ድረ ገጻችን ትኩረት እንዲያደርጉ ለመርዳት የአድራሻ ካርዶችን መጠቀም እንችላለን።