በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ጥሩ መልስ መስጠት የሚቻለው እንዴት ነው?

ጥሩ መልስ መስጠት የሚቻለው እንዴት ነው?

አንድ ሰው ጥሩ መልስ ሲሰጥ ጉባኤውን ያንጻል። (ሮም 14:19) በተጨማሪም ግለሰቡ ራሱ ይጠቀማል። (ምሳሌ 15:23, 28) ስለሆነም በእያንዳንዱ ስብሰባ ላይ ቢያንስ አንድ መልስ ለመስጠት ጥረት ማድረግ ይኖርብናል። እርግጥ ነው እጃችንን ባወጣን ቁጥር እንጠየቃለን ማለት አይደለም። ስለዚህ ከአንድ በላይ መልሶችን መዘጋጀት ጠቃሚ ነው።

ጥሩ መልስ የሚሰጥ ሰው . . .

  • መልሱ ቀላል፣ ግልጽ እና አጭር ነው። አብዛኛውን ጊዜ እንዲህ ያለ መልስ በ30 ሴኮንድ ወይም ከዚያ ባነሰ ጊዜ ውስጥ መስጠት ይቻላል

  • በአብዛኛው በራሱ አባባል ይመልሳል

  • ሌሎች የሰጡትን መልስ አይደግምም

የመጀመሪያውን መልስ እንድትሰጥ ከተጋበዝክ . . .

  • ለጥያቄው አጭርና ቀጥተኛ መልስ ስጥ

ለጥያቄው ቀጥተኛ መልስ ከተሰጠ በኋላ . . .

  • በአንቀጹ ውስጥ ያሉት ጥቅሶች ከነጥቡ ጋር እንዴት እንደሚዛመዱ ተናገር

  • ትምህርቱ ከሕይወታችን ጋር ምን ተያያዥነት እንዳለው ጥቀስ

  • ሐሳቡን እንዴት ተግባራዊ ማድረግ እንደሚቻል አብራራ

  • ነጥቡን የሚያጎላ አጭር ተሞክሮ ተናገር