በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ምሳሌ 12-16

ጥበብ ከወርቅ የተሻለ ነው

ጥበብ ከወርቅ የተሻለ ነው

አምላካዊ ጥበብ ውድ ዋጋ አለው የምንለው ለምንድን ነው? ጥበብ ባለቤቱን ከክፋት ጎዳና የሚጠብቅ ከመሆኑም በላይ ሕይወቱን ያድንለታል። በባሕርይው፣ በአነጋገሩ እንዲሁም በድርጊቱ ላይ በጎ ተጽዕኖ ያሳድራል።

ጥበብ ከኩራት ይጠብቃል

16:18, 19

  • ጥበበኛ ሰው የጥበብ ሁሉ ምንጭ ይሖዋ እንደሆነ ይገነዘባል

  • በተለይ ስኬት ያገኙ ወይም በጉባኤ ውስጥ ተጨማሪ ኃላፊነት የተሰጣቸው ሰዎች ኩራትና ትዕቢት እንዳይጠናወታቸው መጠንቀቅ አለባቸው

ጥበብ አንደበታችንን በጥሩ መንገድ ለመጠቀም ይረዳናል

16:21-24

  • ጥበበኛ ሰው ጥልቅ ማስተዋል ስላለው የሌሎችን መልካም ጎን ለማየትና ስለ እነሱ አዎንታዊ ነገር ለመናገር ይጥራል

  • ጥበብ በሚንጸባረቅበት መንገድ የሚናገር ሰው ንግግሩ ኃይለኛ ወይም ደግነት የጎደለው ሳይሆን አሳማኝ እና እንደማር ጣፋጭ ይሆናል