ከጥቅምት 3-9
ምሳሌ 1-6
መዝሙር 37 እና ጸሎት
የመግቢያ ሐሳብ (3 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች)
ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
“በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን”፦ (10 ደቂቃ)
[የምሳሌ መጽሐፍ ማስተዋወቂያ የተባለውን ቪዲዮ አጫውት።]
ምሳሌ 3:1-4—ታማኝ ፍቅር እና ታማኝነት አሳዩ (w00 1/15 23-24)
ምሳሌ 3:5-8—በይሖዋ ላይ ሙሉ እምነት አዳብሩ (w00 1/15 24)
መንፈሳዊ ዕንቁዎችን በምርምር ማግኘት፦ (8 ደቂቃ)
ምሳሌ 1:7—“ይሖዋን መፍራት የእውቀት መጀመሪያ” የሆነው በምን መንገድ ነው? (w06 9/15 17 አን. 1፤ it-2-E 180)
ምሳሌ 6:1-5—በሚገባ ሳናመዛዝን አንድ ዓይነት የንግድ ስምምነት ውስጥ ብንገባ መውሰድ ያለብን የጥበብ እርምጃ ምንድን ነው? (w00 9/15 25-26)
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ስለ ይሖዋ ምን ያስተምረኛል?
የዚህ ሳምንት የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ ለመስክ አገልግሎት ሊጠቅሙኝ የሚችሉ ምን ነጥቦች ይዟል?
የመጽሐፍ ቅዱስ ንባብ፦ (4 ደቂቃ ወይም ከዚያ በታች) ምሳሌ 6:20-35
በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር
የዚህን ወር መግቢያዎች ተዘጋጅ፦ (15 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። እያንዳንዱን የአቀራረብ ናሙና ቪዲዮ አጫውት፤ ከዚያም ጎላ ባሉ ነጥቦች ላይ ተወያዩ። በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት በሚደረገው ስብሰባ ላይ ሰዎች እንዲገኙ ለመጋበዝ በሚደረገው ዓለም አቀፍ ዘመቻ ላይ እንዲካፈሉ አስፋፊዎችን አበረታታ።
ክርስቲያናዊ ሕይወት
መዝሙር 107
ለጉባኤው እንደሚያስፈልግ ተጠቀሙበት፦ (8 ደቂቃ) አማራጭ፦ በዓመት መጽሐፍ (እንግሊዝኛ) (yb16 25-27) ላይ ተመሥርቶ በውይይት የሚቀርብ። አድማጮች ምን ትምህርት እንዳገኙ ጠይቅ።
በስብሰባዎቻችን ላይ ለሚገኙ ሰዎች መልካም ማድረግ (ምሳሌ 3:27)፦ (7 ደቂቃ) በውይይት የሚቀርብ። በመንግሥት አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የተባለውን ቪዲዮ አጫውት። (ቪዲዮው ስብሰባዎቻችን እና አገልግሎታችን በሚለው ሥር ይገኛል።) ከዚያም በጥቅምት ወር ብቻ ሳይሆን ሁልጊዜም ቢሆን በመንግሥት አዳራሽ ውስጥ ፍቅር የሚንጸባረቅበት መንፈስ እንዲኖር አስተዋጽኦ ማበርከት የምንችለው እንዴት እንደሆነ ጠይቅ።
የጉባኤ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት፦ (30 ደቂቃ) ia ምዕ. 21 አን. 1-12
ክለሳና የቀጣዩ ሳምንት ማስተዋወቂያ (3 ደቂቃ)
መዝሙር 143 እና ጸሎት