“በሙሉ ልብህ በይሖዋ ታመን”
ይሖዋ ሙሉ በሙሉ ልንተማመንበት የሚገባ አምላክ ነው። የስሙ ትርጉምም የገባውን ቃል ሙሉ በሙሉ የመፈጸም ችሎታ እንዳለው ማረጋገጫ ይሆነናል። በይሖዋ ላይ እምነት እንድንጥል ከሚረዱን አስፈላጊ ነገሮች አንዱ ጸሎት ነው። ይሖዋ በእሱ ላይ እምነት ስንጥል ‘ጎዳናችንን ቀና በማድረግ’ እንደሚክሰን በምሳሌ ምዕራፍ 3 ላይ ማረጋገጫ እናገኛለን።
በራሱ አመለካከት ጥበበኛ የሆነ ሰው . . .
-
አስቀድሞ የይሖዋን አመራር ሳይጠይቅ ውሳኔዎችን ያደርጋል
-
በራሱ ወይም በዓለም አስተሳሰብ ይታመናል
በይሖዋ የሚታመን ሰው . . .
-
መጽሐፍ ቅዱስን በማጥናት፣ በማሰላሰል እንዲሁም በመጸለይ ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ዝምድና ይመሠርታል
-
ውሳኔ ሲያደርግ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች በመመርመር የይሖዋን አመራር ይፈልጋል
መጀመሪያ፦ ትክክለኛ የሚመስለኝን ምርጫ አደርጋለሁ |
መጀመሪያ፦ በመጸለይና የግል ጥናት በማድረግ የይሖዋን አመራር እፈልጋለሁ |
ቀጥሎ፦ ይሖዋን ውሳኔዬን እንዲባርክልኝ እጠይቃለሁ |
ቀጥሎ፦ ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር የሚስማማ ውሳኔ አደርጋለሁ |