በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

የአቀራረብ ናሙናዎች

የአቀራረብ ናሙናዎች

ንቁ!

ጥያቄ፦ አንዳንድ ሰዎች፣ ኢየሱስ በእርግጥ በምድር ላይ የኖረ ሰው መሆኑን ይጠራጠራሉ፤ ሌሎች ግን በምድር ላይ መኖሩን እርግጠኞች ናቸው። ‘ስለዚህ ጉዳይ በእርግጠኝነት ማወቅ አይቻልም’ የሚሉ ሰዎችም አሉ። እርስዎስ ምን ይላሉ?

አበርክት፦ ይህ ንቁ! መጽሔት ይህን ጉዳይ አስመልክቶ ማስረጃዎቹ ምን እንደሚያሳዩ ያብራራል።

እውነትን አስተምሩ

ጥያቄ፦ ስንሞት ምን እንሆናለን?

ጥቅስ፦ ዮሐ 11:11-14

እውነት፦ ሰው ሲሞት ከሕልውና ውጪ ይሆናል። ስለዚህ ከሞትን በኋላ ስለምንሆነው ነገር መጨነቅ አያስፈልገንም። ኢየሱስ ሞትን ከእንቅልፍ ጋር አመሳስሎታል። ኢየሱስ ለአልዓዛር እንዳደረገው ሁሉ በሞት ያጣናቸውን ወዳጆቻችንን “በመቀስቀስ” ዳግመኛ በምድር ላይ በደስታ እንዲኖሩ ያደርጋል።—ኢዮብ 14:14

የጉባኤ ስብሰባ መጋበዣ ወረቀት (inv)

አበርክት፦ አንድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ንግግር ላይ እንዲገኙ ብጋብዝዎት ደስ ይለኛል። ንግግሩ የሚቀርበው በዚህ አካባቢ በሚገኝ የመንግሥት አዳራሽ ነው። [የስብሰባ መጋበዣ ወረቀቱን ካበረከትክ በኋላ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት የሚደረገው ስብሰባ የሚካሄድበትን ጊዜና ቦታ ግለጽለት፤ ከዚያም የሕዝብ ንግግሩን ርዕስ ንገረው።]

ጥያቄ፦ ከዚህ በፊት በመንግሥት አዳራሽ ተገኝተው ያውቃሉ? [ሁኔታው አመቺ ከሆነ በመንግሥት አዳራሻችን ውስጥ ምን ይከናወናል? የተባለውን ቪዲዮ አሳየው።]

የራስህን መግቢያ አዘጋጅ

ከላይ የተጠቀሱትን ምሳሌዎች እንደ ናሙና አድርገህ በመጠቀም በመስክ አገልግሎት ላይ የምትጠቀምበት የራስህን አቀራረብ አዘጋጅ።