በማላዊ የሚገኙ ወንድሞች ክርስቲያናዊ ፍቅር ሲያሳዩ

የክርስቲያናዊ ሕይወትና አገልግሎት ስብሰባ አስተዋጽኦ ጥቅምት 2018

የውይይት ናሙናዎች

‘የሰው ልጆች መከራ የሚደርስባቸው ለምንድን ነው? አምላክ መከራን ለማስወገድ ምን ያደርጋል?’ በሚለው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ለመወያየት የሚረዱ የውይይት ናሙናዎች።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኢየሱስ ለበጎቹ ያስባል

ጥሩ እረኛ የሆነው ኢየሱስ ስለ እያንዳንዱ በግ ይኸውም በጉ የሚያስፈልገውን ነገር እንዲሁም ድክመቱንና ጥንካሬውን ያውቃል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኢየሱስን በርኅራኄው ምሰሉት

ኢየሱስ ርኅራኄ ማሳየቱና ራሱን በሌሎች ቦታ ማስቀመጡ አስገራሚ የሆነው ለምንድን ነው?

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

“አርዓያ ሆኜላችኋለሁ”

ኢየሱስ ሐዋርያቱ ትሑት እንዲሆኑ እንዲሁም ዝቅ ተደርገው የሚቆጠሩ ሥራዎችን ለወንድሞቻቸው ሲሉ እንዲያከናውኑ አስተምሯቸዋል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ራስ ወዳድና በቀላሉ የምትበሳጩ አትሁኑ

የክርስቶስ ዓይነት ፍቅር ለማሳየት እንድንችል የሌሎችን ፍላጎት የምናስቀድም እንዲሁም በቀላሉ የማንበሳጭ ሰዎች መሆን ይኖርብናል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

‘የዓለም ክፍል አይደላችሁም’

የኢየሱስ ተከታዮች፣ በዙሪያቸው ያሉት ሰዎች መጥፎ ተጽዕኖ እንዳያሳድሩባቸው ደፋር መሆን ያስፈልጋቸዋል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ውድ የሆነውን አንድነታችንን ጠብቁ

አንድነታችንን ጠብቀን ለመኖር በሌሎች መልካም ጎን ላይ ማተኮር እንዲሁም ሌሎችን በነፃ ይቅር ማለት ያስፈልገናል።

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት

ኢየሱስ ስለ እውነት መሥክሯል

እኛም የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት እንደመሆናችን መጠን በንግግራችንም ሆነ በተግባራችን ስለ እውነት እንመሠክራለን።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ከእውነት ጋር ደስ ይበላችሁ

የምንኖረው በውሸትና በክፋት በተሞላ ዓለም ውስጥ ቢሆንም ስለ እውነት ልንመሠክር እንዲሁም ከእውነት ጋር ደስ ሊለን ይገባል።