በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ከእውነት ጋር ደስ ይበላችሁ

ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ከእውነት ጋር ደስ ይበላችሁ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? የኢየሱስን ምሳሌ በመከተል ስለ አምላክ ዓላማዎች የሚገልጸውን እውነት ማወጅ አለብን። (ዮሐ 18:37) በተጨማሪም የምንኖረው በውሸትና በክፋት በተሞላ ዓለም ውስጥ ቢሆንም ከእውነት ጋር ደስ ሊለን፣ እውነት ልንናገር እንዲሁም እውነት የሆነውን ነገር ልናስብ ይገባል።—1ቆሮ 13:6፤ ፊልጵ 4:8

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ሐሜትን ላለመስማትና ላለማሰራጨት ቁርጥ ውሳኔ አድርግ።—1ተሰ 4:11

  • ሌሎች ጉዳት ሲደርስባቸው አትደሰት

  • አዎንታዊ በሆኑና በሚያበረታቱ ነገሮች ተደሰት

“እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ”—በዓመፅ ሳይሆን ከእውነት ጋር ደስ ይበላችሁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ዴቢ ‘በዓመፅ እንደተደሰተች’ የሚያሳየው ምንድን ነው?

  • አሊስ ከዴቢ ጋር ያደረገችው ጭውውት አዎንታዊ ነገሮች ላይ እንዲያተኩር ያደረገችው እንዴት ነው?

  • ከሌሎች ጋር ልናወራቸው የምንችላቸው አንዳንድ መልካም ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

በዓመፅ ሳይሆን ከእውነት ጋር ደስ ይበላችሁ