በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በቀጥታ ወደ ርዕስ ማውጫው ሂድ

ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 37–38

የማደሪያ ድንኳኑ መሠዊያዎች በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ የነበራቸው ሚና

የማደሪያ ድንኳኑ መሠዊያዎች በእውነተኛው አምልኮ ውስጥ የነበራቸው ሚና

37:25, 29፤ 38:1

የማደሪያ ድንኳኑ መሠዊያዎች የተሠሩት ይሖዋ በሰጠው መመሪያ መሠረት ሲሆን ልዩ ትርጉም ነበራቸው።

  • የይሖዋ አገልጋዮች የሚያቀርቡት ተቀባይነት ያለው ጸሎት ልክ በብልሃት እንደተቀመመ ዕጣን ይሖዋን ያስደስተዋል

  • የሚቃጠል መባ በሚቀርብበት መሠዊያ ላይ የሚቀርቡትን መሥዋዕቶች ይሖዋ ይቀበላቸው ነበር። የሚቃጠል መባ የሚቀርብበት መሠዊያ የአምላክን “ፈቃድ” ይኸውም አንድያ ልጁ ያቀረበውን ፍጹም ሰብዓዊ መሥዋዕት ለመቀበል ያለውን ፈቃደኝነት ያመለክታል። ይህ መሠዊያ የሚገኘው በማደሪያ ድንኳኑ ፊት ለፊት መሆኑ በይሖዋ ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት በኢየሱስ ቤዛዊ መሥዋዕት ላይ እምነት ማሳደር እንደሚያስፈልገን ያስታውሰናል።—ዕብ 10:5-10፤ ዮሐ 3:16-18

ጸሎታችን በአምላክ ፊት እንደተዘጋጀ ዕጣን እንዲሆን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው?—መዝ 141:2