ክርስቲያናዊ ሕይወት
ከይሖዋ ጋር ያላችሁን ዝምድና ከፍ አድርጋችሁ ተመልከቱ
የይሖዋ ምሥክር መሆን ልዩ መብት ያስገኛል። ራሳችንን ወስነን የተጠመቅን ክርስቲያኖች እንደመሆናችን መጠን ከሉዓላዊው ጌታ ከይሖዋ ጋር በግለሰብ ደረጃ የቅርብ ዝምድና መመሥረት ችለናል። ይሖዋ በልጁ አማካኝነት ወደ ራሱ ስቦናል። (ዮሐ 6:44) ጸሎታችንንም ይሰማል።—መዝ 34:15
ከይሖዋ ጋር ያለን ውድ ዝምድና እንዳይበላሽ ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? እንደ እስራኤላውያን የኃጢአት ጎዳና እንዳንከተል መጠንቀቅ ይኖርብናል። እስራኤላውያን ከይሖዋ ጋር ቃል ኪዳን ከገቡ ብዙም ሳይቆይ የወርቅ ጥጃ በመሥራት ጣዖት አምልከዋል። (ዘፀ 32:7, 8፤ 1ቆሮ 10:7, 11, 14) ራሳችንን እንደሚከተለው እያልን መጠየቅ እንችላለን፦ ‘መጥፎ ነገር ለማድረግ ስፈተን ምን ምላሽ እሰጣለሁ? ድርጊቴ ከይሖዋ ጋር ያለኝን ዝምድና ከፍ አድርጌ እንደምመለከተው ያሳያል?’ ለሰማዩ አባታችን ያለን ጥልቅ ፍቅር እሱ ከሚጠላቸው ነገሮች እንድንሸሽ ያነሳሳናል።—መዝ 97:10
ከይሖዋ ጋር ያላችሁ ዝምድና እንዳይበላሽ ተጠንቀቁ (ቆላ 3:5) የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
-
ስግብግብነት ምንድን ነው?
-
ከስግብግብነትና ከጣዖት አምልኮ መራቅ ያለብን ለምንድን ነው?
-
በምንዝርና በጣዖት አምልኮ መካከል ያለው ተመሳሳይነት ምንድን ነው?
-
በተለይ ቲኦክራሲያዊ ኃላፊነት ያላቸው ሰዎች ለትዳር ጓደኛቸው ፍላጎት ትኩረት መስጠት ያለባቸው ለምንድን ነው?