በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ

ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ

የግል መረጃ

Watchtower Bible and Tract Society of New York, Inc. የተባለው ድርጅት ወይም ይህ ድርጅት የሚጠቀምባቸው ሕጋዊ ማኅበራት በዚህ ድረ ገጽ ላይ የምታስገባውን የግል መረጃ የሚጠቀሙበት መረጃውን በሰጠህበት ወቅት ለተስማማህበት ዓላማ ብቻ ነው። Watchtower Bible and Tract Society of New York, Inc. የግል መረጃህን ለማንም አይሰጥም፤ ይሁንና የግል መረጃህን ለሌላ ወገን መስጠት አስገዳጅ የሚሆንባቸው ጊዜያት ይኖራሉ። ለምሳሌ አንተ የጠየቅከውን አገልግሎት እንድታገኝ መረጃህን በአንተ ፈቃድ ለሌላ ወገን ልንሰጥ እንችላለን፤ በተጨማሪም ሕጎችንና ደንቦችን ለማክበር፣ የማጭበርበር ድርጊቶችን ለመመርመርና ለመከላከል እንዲሁም ከደህንነት ወይም ከቴክኒካዊ ጉዳዮች ጋር በተያያዘ የግል መረጃህን መስጠት የግድ አስፈላጊ እንደሆነ ድርጅቱ ሙሉ እምነት በሚኖረው ጊዜ የግል መረጃህን ለሌላ ወገን ሊሰጥ ይችላል። በድረ ገጹ ላይ የምታስገባው ማንኛውም የግል መረጃ በምንም ዓይነት መንገድ አይሸጥም፣ አይለወጥም ወይም አይከራይም።

የኢ-ሜይል አድራሻ

በዚህ ድረ ገጽ ላይ አካውንት ስትከፍት ያስገባኸውን የኢ-ሜይል አድራሻ የምንጠቀመው አካውንትህን በተመለከተ ልናነጋግርህ በምንፈልግበት ጊዜ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ የተጠቃሚ ስምህን ወይም የይለፍ ቃልህን በመርሳትህ ምክንያት ወደ አካውንትህ መግባት አቅቶህ እርዳታ በምትጠይቅበት ጊዜ አንተን የምንረዳው መጀመሪያ ወዳስገባኸው የኢ-ሜይል አድራሻ መልእክት በመላክ ነው።

ኩኪዎች

ኩኪዎች የሚያገለግሉት ተጠቃሚው ድረ ገጹን በሚጠቀምበት ወቅት የመረጣቸውን ነገሮች ለማስታወስ ነው። ለምሳሌ ያህል፣ ተጠቃሚው ድረ ገጹን በሚቃኝበት ጊዜ የመረጠውን ቋንቋ መዝግቦ በመያዝ በሚቀጥለው ጊዜ በድጋሚ ወደ ድረ ገጹ ሲገባ በዚያ ቋንቋ እንዲከፍትለት የሚያደርገው ኩኪ ነው። ኩኪዎች ማንኛውንም የግል መረጃ አይሰበስቡም እንዲሁም አያስቀምጡም።

አክቲቭ ስክሪፕቲንግ ወይም ጃቫስክሪፕት

የስክሪፕቲንግ ዓላማ ድረ ገጹ የሚሠራበትን ቅልጥፍና ከፍ ማድረግ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ ድረ ገጹ መረጃዎችን በፍጥነት ለተጠቃሚው ለማሳየት እንዲችል ይረዳዋል። ድረ ገጹ በተጠቃሚዎች ኮምፒውተር ላይ ፕሮግራሞችን ለመጫን ወይም ያልተፈቀደለትን መረጃ ከተጠቃሚው ለመሰብሰብ ፈጽሞ ስክሪፕቲንግ አይጠቀምም።

አንዳንድ የድረ ገጹ ክፍሎች በተገቢው መንገድ እንዲሠሩ አክቲቭ ስክሪፕቲንግ ወይም ጃቫስክሪፕት ማሰሻው (browser) ላይ መብራት ይኖርበታል። አብዛኞቹ የኢንተርኔት ማሰሻዎች ለተወሰኑ ድረ ገጾች አክቲቭ ስክሪፕቲንግ ወይም ጃቫስክሪፕትን ለማብራትና ለማጥፋት የሚያስችል አማራጭ ይሰጣሉ። ለአንዳንድ ድረ ገጾች አክቲቭ ስክሪፕቲንግን ወይም ጃቫስክሪፕትን እንዴት ማብራት እንደሚቻል ለማወቅ የኢንተርኔት ማሰሻውን የእገዛ ፋይሎች ተመልከት።

የግል ሚስጥር ፖሊሲያችንን መቀየር አስፈላጊ በሚሆንበት ጊዜ ለውጦቹን በዚህ ገጽ ላይ እናወጣለን፤ ይህም ምን ዓይነት መረጃዎችን እንደምንሰበስብና መረጃዎቹን ለምን ዓላማ እንደምንጠቀምባቸው ለማወቅ ይረዳሃል።