ጥቅምት 18, 2024
አዲስ ነገር
አገልግሎታቸውን ማስፋት ከሚፈልጉ ክርስቲያኖች የሚጠበቀው የዕድሜ ገደብ መስተካከሉ በዓመታዊ ስብሰባ ላይ ተነገረ
የድርጅቱ ሕጋዊ ማኅበር ጥቅምት 5, 2024 ባካሄደው ዓመታዊ ስብሰባ ላይ በተነገረው ማስታወቂያ መሠረት በቤቴል ወይም በቲኦክራሲያዊ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ ለማገልገል ከሚያመለክቱ ክርስቲያኖች የሚጠበቀው ዝቅተኛ ዕድሜ ከ19 ወደ 18 እንዲቀንስ ተደርጓል። በተጨማሪም ከመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት አመልካቾች የሚጠበቀው ዕድሜ ከ23 ወደ 21 ዝቅ ብሏል።
እነዚህ አስደሳች ማስተካከያዎች ወዲያውኑ ተፈጻሚ ይሆናሉ። ይህን ለውጥ ተከትሎ ብቃቱን ያሟሉ ወጣት ወንድሞችና እህቶች፣ ለይሖዋ የሚያቀርቡትን አገልግሎት ማስፋት የሚችሉባቸው ተጨማሪ አጋጣሚዎች ይከፈቱላቸዋል።