በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

በሄይቲ በተከሰተው የምድር ነውጥ የፈረሰ የአንድ ወንድም ቤት

ነሐሴ 18, 2021
ሄይቲ

ሄይቲ በከባድ የምድር ነውጥ ተመታች

ሄይቲ በከባድ የምድር ነውጥ ተመታች

ነሐሴ 14, 2021 በመሬት መንቀጥቀጥ መለኪያ 7.2 የተመዘገበ የምድር ነውጥ ደቡብ ምዕራባዊ ሄይቲን መታ፤ ይህን ተከትሎም ትናንሽ ነውጦች ተከስተው ነበር። የምድር ነውጡ ያስከተለው ጉዳት ገና እየተጠና ነው።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • የሚያሳዝነው 2 እህቶችና 1 ወንድም ሕይወታቸውን አጥተዋል

  • 21 ወንድሞችና እህቶች የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 119 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 72 ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል

  • 5 የስብሰባ አዳራሾች አነስተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል

  • 4 የስብሰባ አዳራሾች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • አንድ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ የእርዳታ ሥራውን እያደራጀ ነው። ኮሚቴው አደጋው በደረሰበት አካባቢ ከሚያገለግሉት 2 የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና ከጉባኤ ሽማግሌዎች ጋር በመተባበር ተግባራዊ እርዳታና እረኝነት እያደረገ ነው

  • የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴው እንደ ብርድ ልብስ፣ ልብስ፣ ምግብ፣ መድኃኒት፣ መጠለያ ሸራ እና ውኃ ያሉ የእርዳታ ቁሳቁሶችን የማከፋፈሉን ሥራ እያስተባበረ ነው። ጉዳት የደረሰባቸው ወንድሞችና እህቶች የሕክምና እርዳታ እንዲያገኙም ዝግጅት ተደርጓል

  • ሁሉም የእርዳታ ሥራዎች እየተከናወኑ ያሉት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ የወጡትን የደህንነት ደንቦች ባገናዘበ መልኩ ነው

ሁኔታው አስቸጋሪ ቢሆንም ጉዳት በደረሰበት አካባቢ ያሉት አብዛኞቹ ጉባኤዎች የሳምንቱ መጨረሻ ስብሰባቸውን እሁድ፣ ነሐሴ 15 በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካኝነት ማድረግ ችለዋል። በተጨማሪም ወንድሞችና እህቶች “በእምነት ብርቱ ሁኑ!” የተባለውን የክልል ስብሰባ የእሁድ ጠዋት ፕሮግራም ተመልክተዋል።

የእምነት ባልንጀሮቻችንን በሞት ስላጣን በእጅጉ አዝነናል። ሐዘን ለደረሰባቸው እንዲሁም በምድር ነውጡ የተነሳ አካላዊና ስሜታዊ ጉዳት ለደረሰባቸው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን እንጸልያለን። ይሖዋ ሥቃያቸውን እንደሚመለከትና በዚህ የጭንቅ ጊዜ መጠጊያና ብርታት እንደሚሆንላቸው እንተማመናለን።—መዝሙር 46:1, 2