ሰኔ 15, 2023
ሄይቲ
ሄይቲ በጎርፍ ተጥለቀለቀች
ሰኔ 2 እና 3, 2023 የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ የሄይቲ አንዳንድ አካባቢዎች በጎርፍ ተጥለቅልቀዋል። ሪፖርቶቹ እንደሚያሳዩት በጎርፍ መጥለቅለቁ በአሥር ሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች የተጎዱ ሲሆን በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች የሚገኙ ወደ 40,000 የሚጠጉ ቤተሰቦች የአደጋው ሰለባ ሆነዋል። ከ13,500 የሚበልጡ ሰዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል። ቢያንስ 50 ሰዎች ሞተዋል።
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
በአደጋው የሞተ የይሖዋ ምሥክር የለም
አንድ ወንድምና አንዲት እህት ጉዳት ደርሶባቸዋል
60 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
1 መኖሪያ ቤት ወድሟል
3 ቤቶች ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸዋል
19 ቤቶች ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል
ጉዳት የደረሰበት የስብሰባ አዳራሽም ሆነ ቲኦክራሲያዊ ሕንፃ የለም
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና በአካባቢው የሚገኙ የጉባኤ ሽማግሌዎች አደጋው በደረሰበት አካባቢ ለሚገኙ ወንድሞችና እህቶች መንፈሳዊና ቁሳዊ እርዳታ እያደረጉ ነው
በአገሪቱ የሚገኙ ጉባኤዎች በእርዳታ ሥራው እያገዙ ነው
ይሖዋ፣ በሄይቲ የጎርፍ መጥለቅለቅ ለተጎዱ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ‘ብርታት እንደሚሰጣቸው’ እርግጠኞች ነን።—መዝሙር 29:11