በቀጥታ ወደ ዋናው ጉዳይ ግባ

ፖርት ኦ ፕራንስ፣ ሄይቲ ውስጥ መንገድ ለመዝጋት የተቃጠሉ ጎማዎች

መጋቢት 19, 2024
ሄይቲ

አለመረጋጋት ተባብሶ በቀጠለባት በሄይቲ የሚኖሩ ወንድሞች

አለመረጋጋት ተባብሶ በቀጠለባት በሄይቲ የሚኖሩ ወንድሞች

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሄይቲ እየጨመረ የመጣው የወሮበሎች ጥቃት እና አለመረጋጋት በአገሪቱ ላሉ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ፈተና ሆኗል። መጋቢት 2, 2024 ታጣቂ ቡድኖች በቁልፍ መሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ከሰነዘሩበት ጊዜ አንስቶ በሄይቲ ዋና ከተማ በፖርት ኦ ፕራንስ አለመረጋጋትና ወንጀል ነግሧል። መንግሥት የሰዓት እላፊና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አውጇል። ሪፖርቶች እንደሚጠቁሙት 15,000 ገደማ ሰዎች ለደህንነታቸው ሲሉ መኖሪያቸውን ጥለው የሸሹ ሲሆን በርካቶች ተገድለዋል።

በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት

  • ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል ሕይወቱን ያጣ ወይም ጉዳት የደረሰበት የለም

  • 113 ወንድሞችና እህቶች መኖሪያቸውን ጥለው ለመሸሽ ተገደዋል

  • 2 መኖሪያ ቤቶች ወድመዋል

  • 5 ቤተሰቦች ንብረታቸውን ሙሉ በሙሉ ተዘርፈዋል

  • ጉዳት የደረሰበት ወይም የወደመ የስብሰባ አዳራሽ የለም

የእርዳታ እንቅስቃሴ

  • 4 የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴዎች በመላው የቅርንጫፍ ቢሮው ክልል የእርዳታ እንቅስቃሴዎችን እንዲያስተባብሩ ተመድበዋል

  • የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች ሸሽተው የሄዱትን ጨምሮ ጉዳት ለደረሰባቸው ወንድሞችና እህቶች መንፈሳዊና ቁሳዊ ድጋፍ እያቀረቡ ነው

ይሖዋ ለሄይቲ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በዚህ አስጨናቂ ጊዜ ጥበብና የተረጋጋ ልብ እንዲሰጣቸው መላው የወንድማማች ማኅበር እየጸለየ ነው። እኛም እንደነሱ ‘ሰላም የሚበዛበትን’ አዲስ ዓለም በጉጉት እንጠባበቃለን።​—መዝሙር 72:7