ነሐሴ 17, 2020
ሜክሲኮ
ሐና የተባለችው አውሎ ነፋስ ሜክሲኮን መታች
ቦታ
ታማውሊፓስ ግዛት እና ኑዌቮ ሊዮን ግዛት፣ ሜክሲኮ
የደረሰው አደጋ
ሐና የተባለችው አውሎ ነፋስ ሐምሌ 26, 2020 ሰሜን ምሥራቃዊ ሜክሲኮን የመታች ሲሆን በአካባቢው የጎርፍ መጥለቅለቅ እንዲከሰት አድርጋለች
በወንድሞቻችንና በእህቶቻችን ላይ የደረሰ ጉዳት
በኑዌቮ ሊዮን ግዛት 14 ቤተሰቦች ለጥንቃቄ ሲባል ቤታቸውን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል
በታማውሊፓስ ግዛት በምትገኘው ሬይኖሳ ከተማ 100 አስፋፊዎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
በንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት
በኑዌቮ ሊዮን ግዛት 21 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል
በታማውሊፓስ ግዛት 117 ቤቶች ጉዳት ደርሶባቸዋል
የእርዳታ እንቅስቃሴ
የማዕከላዊ አሜሪካ ቅርንጫፍ ቢሮ የአደጋ ጊዜ እርዳታ አስተባባሪ ኮሚቴ አቋቁሟል
ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች ያሉ የወረዳ የበላይ ተመልካቾችና የጉባኤ ሽማግሌዎች በጎርፍ የተጥለቀለቁትን ቤቶች ቆሻሻ የማስወገድና በፀረ ጀርም ኬሚካል የማጽዳት ሥራ እያስተባበሩ ነው
በኑዌቮ ሊዮን ግዛት ከቤታቸው እንዲወጡ ከተደረጉት ወንድሞችና እህቶች መካከል አብዛኞቹ ወደ ቤታቸው መመለስ ችለዋል
በታማውሊፓስ ግዛት በጎርፉ ለተጠቁት አስፋፊዎች በአካባቢው የሚገኙ ጉባኤዎች ምግብና ልብስ እያቀረቡላቸው ነው
ከወንድሞቻችንና ከእህቶቻችን መካከል አካላዊ ጉዳት የደረሰበት ባለመኖሩ ይሖዋን እናመሰግናለን። እየተካሄደ ያለው የእርዳታ እንቅስቃሴ በሰማይ ያለው አባታችንና ሕዝቡ ‘በጭንቅ ጊዜ ፈጥነው የሚደርሱ ረዳቶች’ መሆናቸውን ያረጋግጣል።—መዝሙር 46:1